Textile, Garments and Uniforms

የአቡነ ባስልዮስ አጠቃላይ 2ኛ ደ/ት/ቤት የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ የህትመት ሥራዎች፣ የህክምና እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ የፅዳት እቃዎች፣ የጥገና እቃዎች፣ ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ተገጣጣሚ ቋሚ እቃዎች፣ የመስተንግዶ እቃዎች የተለያዩ፣ የኤሌክትሮኒክስ፣ ኤሌክትሪክና የኢንተርኔት መስመር ጥገና ሥራዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ 001/2019

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ በወረዳ 01 የአቡነ ባስልዮስ አጠቃላይ 2ኛ ደ/ት/ቤት በ2019ዓ.ም የሥራ ዘመን በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡-

  • ሎት 1፡ የደንብ ልብስ፣
  • ሎት 2፡ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
  • ሎት3፡- የህትመት ሥራዎች፣
  • ሎት፡-4 የህክምና እቃዎች፣
  • ሎት5፡- አላቂ የትምህርት እቃዎች፣
  • ሎት 6፡- የፅዳት እቃዎች፣
  • ሎት7 ፡ የጥገና እቃዎች፣
  • ሎት8፡ ቋሚ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • ሎት9፡- ተገጣጣሚ ቋሚ እቃዎች፣
  • ሎት 10፡- የመስተንግዶ እቃዎች የተለያዩ፣
  • ሎት 11፡- የኤሌክትሮኒክስ፣ ኤሌክትሪክና የኢንተርኔት መስመር ጥገና ሥራዎች

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርት የምታሟሉ ማንኛውም የዘርፉ ህጋዊ ነጋዴዎች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. በዘርፉ ሕጋዊና የታደሰ ንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በጥቃቅንና አነስተኛ ተደራጅተው ለሚመጡ የበላይ ኃላፊ የተፈረመ ደብዳቤ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አየር ጤና ቻይና ካምፕ ወደ ዘነበወርቅ መነሃሪያ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የአቡነ ባስልዮስ አጠቃላይ 2ኛ ደ/ት/ቤት ግዥ ቢሮ ቁጥር 4 ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 100/አንድ መቶ/ ብር ብቻ ከፍለው መግዛት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት1 ለሎት6፤ ለሎት8 እና ለሎት9 ለእያንዳንዳቸው 5000/አምስት ሺህ ብር/፣ ለሎት2 ፤ለሎት3 ፤ለሎት4፤ለሎት5 ለሎት7 ለእያንዳንዱ 4000/አራት ሺህ ብርለሎት 10 እና 11 3000/ሶስት ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
  4. ተጫራቾች ለእያንዳዱ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ 1 ቀን ቀደም ብሎ የድርጅቱን ሙሉ ስምና ሕጋዊ ማህተም በማድረግ ግዥ በሮ ቁጥር 4 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  5. ገዢው አካል የሚገዛውን ዕቃ እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
  6. በጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊ መሆኑ ሲረጋገጥ ውል ለመዋዋል ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ለውል ማስከበሪያ በሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል።
  7. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ የጨረታው ሳጥን ታሽጐ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  9. የእቃ ማጓጓዣ አሸናፊው ድርጅት ይሸፍናል።
  10. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ : አየር ጤና ቻይና ካምፕ ወደ ዘነበወርቅ መነሃሪያ በሚወስደው መንገድ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09-24 84 41-42 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ

በኮልፌ ቀራንዮ ክ/ከ ት/ጽ/ቤት የአቡነ ባስልዮስ አጠቃላይ 2ኛ ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-28
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-28 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ የሥራ ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Abune Basilios Secondary School
  • Buyer address: ኮ/ቀ/ክ/ከተማ አቡነ ባስልዮስ የ2ኛ ደ/ት/ቤት ወይም በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T10:07:45.000Z
← Back to all tenders