Vehicle and Machinery Foreclosure

ንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ያገለገሉ አይቬኮና ሲኖ ትራክ ከባድ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች የመጫን አቅም ክብደት 400 (አራት መቶ) ኩንታል የሆኑትን ባሉበት ሁኔታ ተጫራቾች አይተዋቸው በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ፣

ንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ያገለገሉ አይቬኮና ሲኖ ትራክ ከባድ የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች የመጫን አቅም ክብደት 400 (አራት መቶ) ኩንታል የሆኑትን ባሉበት ሁኔታ ተጫራቾች አይተዋቸው በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያው ከወጣበት ነሀሴ 12 ቀን 2018 እስከ ነሀሴ 26 ቀን 2018 ጠዋት 3፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ስለ አሻሻጡ የሚገልፀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል ከፋይናንስ ቢሮ ማግኘት ይችላሉ።

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 1,000,000.00 (አንድ ሚሊዮን ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) አሰርተው ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

ጨረታው ነሀሴ 26 ቀን 2018 ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል።

ንፋስ ስልክ ቀለም ፋብሪካ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
ሳር ቤት አካባቢ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ከጨፌ ኦሮሚያ ቢሮ ፊት ለፊት ጄ ኤፍ ኬ አፓርትመንት 8ኛ ፎቅ
የበለጠ ለመረዳት ስልክ ቁጥር
09 64 75 56 62/ 09 11 65 15 48/ 09 03 00 46 12


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-01 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Nifas Silk Paint Factory
  • Bid bond: ብር 1,000,000.00 (አንድ ሚሊዮን ብር)
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: 2merkato.com (Aug 18, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T11:35:05.000Z
← Back to all tenders