Metal and Metal Working

በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ለጥገና ሥራ የሚያስፈልጉ የብረታብረትና የውሃ ዕቃዎች ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ለጥገና ሥራ የሚያስፈልጉ የብረታብረትና የውሃ ዕቃዎች ግዥን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፡

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ ሆነው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።

2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ብቻ በማሠራት ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ አስር ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ ዋናና ቅጅ ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኢንተርፕራይዙ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ጨረታውን መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በተገኙበት ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 በግልጽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ወይም በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓትና ቦታ በግልፅ ይከፈታል፡፡ /ትክክለኛው የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል።

6. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።

7. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን /+251 925 750 633 / 0913 497 204 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች አንተርፕራይዝ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-26
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
  • Bid opening: 2026-08-26 12:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ሥራዎች ኢንተርፕራይዝ
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T12:01:51.000Z
← Back to all tenders