House Furniture
ኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር ለተለያዩ ዓይነት የፈርኒቸር ግበአቶች(ጥሬ እቃዎች) እና ተያያዥ አክሰሰሪዎች በጨረታ ሰነድ በተዘረዘረው መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ቁጥር 006/2018
የፈርኒቸር ግበቶች(ጥሬ እቃዎች) እና ተያያዥ አክሰሰሪዎች ግዥ የወጣ የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ድርጅታችን ኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር ለተለያዩ ዓይነት የፈርኒቸር ግበአቶች(ጥሬ እቃዎች) እና ተያያዥ አክሰስሪዎች በጨረታ ሰነድ በተዘረዘረው መሠረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን በማሟላት መወዳደር የሚትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. የታደሰ የዘርፉ ንግድ ሥራ ፈቃድ
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር
3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት
4. የተጨማሪ እሴት ታክሰ ከፋይ ምዝገባ የምስክር ወረቀት
5. ተጨራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ 2% የጨረታ መስከበሪያ ዋስትና በሲፒኦ ማሰያዝ አለባቸው፡፡
6. ጨረታው በሁለት ኤንቨሎፕ የሚካሄድ በመሆኑ ተጨራቾች የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ኦፈር ሰነዶችን ለብቻ በመስኮት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማሰገባት አለባቸው፡፡
7. የእቃዎችን ናሙና (ሳምፕስ) ማቅረብ አለባቸው፡፡
ከላይ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች የምታሟሉ ተጫራቾች ይህ ማሰታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስር የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ አዲስ አበባ አደይ አበባ አከባቢ ከባቡር መስመር 30 ሜትር ገባ ብሎ ከሚገኘው ኢካፍኮ አ/ማህበር መ/ቤት ሽያጭ ክፍል ብር 500 (አምስት መቶ) መግዛት የሚችሉ መሆኑን እያሳቅን፤ የጨረታ ሰነደ ሳጥን በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ትንሹ አደራሽ የሚከፈት መሆኑን አውቀው የጨረታ ሰነድ በመግዛት መወዳደር ይችላሉ፣ ሌሎች መስፈርቶች ከጨረታው ሌሎች ሰነደ ማግኘት ይችላሉ፡፡
አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁ.0114 420 675 ወይም 0114 423 035
ኢካፍኮ አክሲዮን ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-08-28
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-08-28 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: ECAFCO S.C.
- Buyer address: ECAFCO S.C Addis AbabaEthiopia
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T12:12:43.000Z