Stationery

በቡኖ በደሌ ዞን ጮራ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዘመን በሥራ ላይ ላሉት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር WM/A/C 8/2018

በቡኖ በደሌ ዞን ጮራ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዘመን በሥራ ላይ ላሉት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  • 1. የጽህፈት መሣሪያዎችና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች
  • 2. የተለያዩ የሰራተኛ የደምብ ልብሶች
  • 3. የቢሮ ውስጥ ቋሚ ዕቃዎች
  • 4. የመኪና እና የሞተር ሳይክል ጎማዎች
  • 5. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች
  • 6. የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ የማስተማሪያ ዕቃዎች
  • 7. የሞተር ሳይክሎች የመኪና ዘይትና ቅባቶች
  • 8.የውሃ መ/ቤት የግንባታ ዕቃዎች

በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

1. ከሚገዙት ዕቃዎች ጋር ተያያዥነት ያለው ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለው።

2. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

3. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

4. ከሚያቀርቡበት ጠቅላላ ዋጋ 5 % /ፐርሰንት/ በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ /CPO/ ማቅረብ የሚችል።

5. አሸናፊ ተጫራቾች ለመልካም የስራ አፈጻጸም የጠቅላላ ዋጋ 10 (ፐርሰንት) ማስያዝ ይኖርበታል።

6. ጨረታው በአየር ላይ የሚውለው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ10 የሥራ ቀናት ሲሆን በ12/12/2018 ዓ.ም በ4:00 ሰዓት ላይ አሰገብተው በ26/12/2018 ዓ.ም 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጮራ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል፡፡

7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 1089 (አንድ ሺህ ሰማኒያ ዘጠኝ) በቴሌብር አካውንት በመክፈል ከጮራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 /አምስት/ መግዛት ይቻላል።

8.ከጠቅላላ ሽያጭ ዋጋ 3 ፐርሰንት ለመቁረጥ ፍቃደኛ የሆነ።

9.የዕቃው ማስረከቢያ ቦታ ጮራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ሆኖ ጠቅላላ ወጪ የሻጩ ግዴታዎች መሆኑን ያመነ።

10የዕቃው ብዛት ሃያ በመቶ ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል።

11.ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ዝርዝር ሠነድ ዋጋ በትክክል በመሙላት በሁለት በተለያዩ ፖስታዎች ኦሪጂናል እና ኮፒውን በማሸግ ማቅረብ አለበት።

12.የታደሰ የንግድ ፍቃድ ኦሪጂናል እና ኮፒ፣ የቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ኦሪጂናል እና ኮፒ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ መሆኑን ማስረጃ ኦሪጂናል እና ኮፒ ፤የቲን ተመዝጋቢነት ማስረጃ ኦርጂናል እና ኮፒ እና ሌሎችንም የተለያዩ ደጋፊ ማስረጃዎችን ኦሪጂናል እና ኮፒውን በሁለት የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ ማቅረብ አለበት።

13. ሲፒኦ / CPO/ ለብቻው በታሸገ አንድ ፖስታ መቅረብ አለበት፡፡

14. አሸናፊው ያሸነፈውን ዕቃ ጥራቱን የጠበቀና ኦሪጂናል ዕቃ ማቅረብ አለበት ጥራቱን ያልጠበቀ አሪጂናል ያልሆነና ያልታዘዘ ዕቃ ካመጣ የመመለስ (የመቀየር) ግዴታ ያለበት መሆኑን ያመነበት፡፡

15. ማንኛውም ውድድር የሚከናወነው በነጠላ ዋጋ ይሆናል፤

16. ዋስትና መስጠት የሚችል መሆን አለበት፡፡

17. ማንኛውም ተጫራች ለደንብ ልብሶች ናሙና ማቅረብ አለበት፡፡

18. ተጫራቾች አንዱ በሌላው ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ መሆኑን እንገልፃለን።

19. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዜዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት አለው፡፡

ለበለጠ መረጃ ጮራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
የስልክ ቁጥር
04 73 37 06 11
047 337 00 45
0910 04 99 72
በቡኖ በደሌ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት የጮራ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): በ12/12/2018 ዓ.ም በ4:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-01 12:00
  • Bid opening (note): በ26/12/2018 ዓ.ም 4:30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Buno Bedele Chora Woreda FEDB
  • Bid bond: 5%
  • Bid document price: 1089 (አንድ ሺህ ሰማኒያ ዘጠኝ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T12:16:15.000Z
← Back to all tenders