House Furniture

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት በመደበኛ በጀት ለሚገዛቸው የእስቴሽነሪ ማቴሪያሎች፤ ፈርኒቸር፤ የፅዳት እቃ፤ ኤሌክትሮኒክስ፤ የመኪና ማቴሪያል ግዥ ህጋዊ ፍቃድ ካላችው ድርጅቶች ላይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ግ/ጨ/01/2019 ዓ.ም

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 በጀት አመት በመደበኛ በጀት ለሚገዛቸው የእስቴሽነሪ ማቴሪያሎች፤ ፈርኒቸር፤ የፅዳትእቃ፤ ኤሌክትሮኒክስ፤ የመኪና ማቴሪያል ግዥ ህጋዊ ፍቃድ ካላችው ድርጅቶች ላይ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች

1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ የዘመኑ ግብር የከፈሉና የተሟላ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2. ግብይቱ 200000 ሺ ብር በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡

3. የTIN No ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም የንግድ ምዝገባ ቁጥርና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሀሳብ መስጫ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡

5. የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡

6. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ ሆኖ ለወደፊት በመንግስት የሚወጣ ጨረታ እንዳይሳተፍ ሲደረግ ይችላል፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የክፊያና ሂሳብ ደጋፊ የስራ ሂደት ማግኘት ይችላሉ::

8. የሚገዙትን ማቴሪያሎች ዝርዝር መግለጫ (እስፔስፊኬሽን) ከሠነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

9. ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ዋናውና ኮፒውን ብቻ ለብቻ ከሁሉም የንግድ ማስረጃዎቻቸው ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፡፡

10. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ከ 11/12/2018 አስከ 26/12/2018 ዓ.ም ድረስ ለተከታታይ ለ15 ቀናት አየር ላይ የሚውል ሲሆን 16ኛው ቀን ማለትም 26/12/2018 በ4፡00 ሰዓት የሚታሸግ ይሆናል፡፡

11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት በዚሁ ቀን 26/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡30 በጨ/ሮ ከ/አስ/ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 በግልፅ የሚከፈት ሲሆን ምናልባት 16ኛው ቀን የህዝብ በዓል ወይም ከመንግስት የስራ ቀን ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 1% በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንት (C.P.O) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

12. የጨረታ ማስከበሪያ ሰዓት ካለፈ በኋላ የመጣ የጨረታ ሠነድ ከጨረታ ሳጥን ውስጥ ሳይገባ ተመላሽ ይሆናል፡፡

13. መ/ቤቱ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፦

  • መ/ቤቱ ግዥውን በነጠላ ዋጋ ወይም በሎት ሊያወዳድር ይችላል፡፡
  • ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0912 120 388 / 0930 811 649/ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  • አድራሻችን ጨፋ ሮቢት ከተማ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ መስመር 300 ኪ/ሜ ላይ እንገኛለን፡፡

በአብክመ በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-01 10:30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Chefa Robit City Administration Finance office
  • Bid bond: 1%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T12:30:31.000Z
← Back to all tenders