Food and Beverage
ገነት ሆቴል የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ የበሬና የበግ ተዋጽኦ፣ የዶሮና የዓሣ ተዋጽኦ እና አትክልትና ፍራፍሬ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሥጋ፣ የዶሮ፣ የዓሣ፣
ለአትክልትና ፍራፍሬ የጨረታ ማስታወቂያ
ገነት ሆቴል የጥራት ደረጃቸውን የጠበቁ የበሬና የበግ ተዋጽኦ፣የዶሮና የዓሣ ተዋጽኦ እና አትክልትና ፍራፍሬ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ትችላላችሁ።
- የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት፣
- በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ፣
- ከዚህ በፊት ከድርጅታችን ጋር የውል ስምምነት የነበረው ከሆነ መልካም ሥራ አፈጻጸም ያለው፡፡
- ተጫራቾች ስለጨረታው የተሟላ ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከድርጅታችን ፋይናንስ ክፍል በብር 300.00(ሦስት መቶ ብር) መግዛት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የምግብ ግብዓት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ለገነት ሆቴል በሚል በማሰራት ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ አስተዳደርና የሰው ኃብት ልማት ዋና ክፍል በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የፋይናንስ ፕሮፖዛሉ ዋጋ በሰነዱ ላይ በግልጽ ካልተገለፀ በስተቀር ተጨማሪ እሴት ታክስ እንደጨመረ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል። 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ ጨረታው ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8:30 ይከፈታል።
- አንድ ተጫራች በሚያቀርበው ዋጋ ላይ ተመስርቶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም::
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በክፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ 0939 500 000
የገነት ሆቴል አስተዳደር
Tender details
- Deadline: 2026-08-26
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-26 14:30
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Genet Hotel Administration
- Buyer address: አ/አ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ላይ ገነት ሆቴል ግቢ ውስጥ
- Bid bond: 5,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T12:33:06.000Z