Vehicle and Machinery Foreclosure
አልቪማ የምግብ አምራች ኃ.የተ.የግ.ማህበር ያገለገለ ጣልያን አይቪኮ ተሽከርካሪ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የተሽከርካሪ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/ የም/አም/ኃ/የተ/የግ/ማህበር ሽያጩ /0005/2026
አልቪማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር የ2020 ሞዴል ያገለገለ ጣልያን አይቪኮ (Model 50C15/53 Year:2020 Chassis no.: EBPBCAHAALD000016: Motor no..FlCE3481j38273261 Clour: White Vehicle type: Bus፣ CC: 2998 ተሽከርካሪን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በዚህም መሠረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት መጫረት ይችላሉ።
1. ማንኛውም የመጫረት ፍላጎት ያለው, በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላል።
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ሲያቀርቡ ለተጫረቱበት ተሽከርካሪ የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 10 % (አስር በመቶ) በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ከሲፒኦ ዉጪ የሚያቀርቡ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
3. የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ተሽከርካሪው አዳማ በሚገኘው የድርጅቱ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ በአካል በመቅረብ ማየት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ አሸናፊው ተለይቶ ከታወቀ በኃላ የሚመለስ ይሆናል።
5. የጨረታው አሸናፊ ለተሽከርካሪው የሚከፈሉ ማንኛውንም የመንግስት ክፍያዎችን ሁሉ ይሸፍናል።
6. ማንኛውም ተጫራትች ሌሎች በሰጡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።
7. የጨረታው አሸናፊ መሆኑ የተገለፀለት ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው 10% (አስር በመቶ) እንደውል ማስከበሪያ ይቆጠራል። የጨረታው አሸናፊ የገባውን ውል ካልፈፀም ለጨረታ መስከበሪያ የተያዘው ዋስትና እንደ ውል ማስከበሪያ ተቆጥሮ የተያዘዉን ገንዘብ አልቪማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ወደ ራሱ ካዝና ገቢ ያደርጋል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከድርጅቱ ፋይናንስ መምርያ አዳማ ወይንም አዲስ አበባ ከሚገኘው ቢሮ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
9. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ 16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን አዳማ ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ከቀኑ በ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ለጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተሞላ ወይንም በሌላ ወረቀት ላይ የተሞላ ዋጋ ተቀባይነት የለውም።
11. የጨረታው አሸናፊ የሚለየው ባቀረበው የመግዣ ዋጋ መሠረት ብቻ ነው።
12. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በተገለጸ በ7 ቀናት ዉስጥ በአካል ቀርቦ ውል መፈፀም አለበት።
13. የጨረታው አሸናፊ ውል እንዲፈፅም በተገለፀለት በ 7 ቀናት ውስጥ ቀርቦ ውል ባይፈፅም ድርጅቱ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘውን ዋስትና ወደ ራሱ ካዝና ገቢ ያደርጋል።
14. ድርጅቱ የተሸለ መንገድ ካገኘ ጨረታን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፤-09 30 29-36 26
አልቪማ የምግብ አምራች ኃ/የተ/የግ/ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-09-02
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ 16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-02 14:30
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ለ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ 16ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ 8፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Alvima Foods Complex PLC
- Buyer TIN: 0023572660
- Bid bond: 10%
- Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T13:09:05.000Z