Spare Parts and Car Decoration Materials
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ለማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውል የሎደር እና የግሬደር ጎማ እንዲሁም ካሜራ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ ቤት ለማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውል
- ሎት 01 የሎደር እና የግሬደር ጎማ እና
- ሎት 02 ለመንግስት ኮምንኬሽን አገልግሎት የሚውል ካሜራ በመስኩ ፍቃድ ያላቸውን ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም፡-
- ሎት 01 የሎደር እና የግሬደር ጎማ
- ሎት 02 ካሜራ
በመስኩ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
የንግድ ምዝገባ ምስክር ያላቸው
ቲን ነምበር ያላቸው
የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የምትችሉ
በመንግስት ግዢ ለመሳተፍ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ የምትችሉ
የጨረታ ዋስትና የሎደር እና የግሬደር ጎማ 50,000 እና ካሜራ 25,000 በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችሉ ተጫራቾች ሰነዱን ከወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በመምጣት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10/አስር ቀን/ ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 መገኘት በሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የተሞላው ዋጋ መግለጫ ካልተሰጠበት ከነቫት ተደርጎ ይወሰዳል።
ለበለጠ መረጃ
046 771 0211 ይደውሉ
በስልጤ ዞን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-08-29
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10/አስር ቀን/ ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-29 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10/አስር ቀን/ ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Silte Zone Worabe City Administration FEDB
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 18, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T13:44:58.000Z