Printing and Publishing
ጣምራ ለማህበራዊ ልማት ድርጅት በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ ክልል እየተገበረ ለሚገኘው ፕሮጀክቶች የሚውል የህትመት አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶችን ለማወዳደር ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ጣምራ ለማህበራዊ ልማት ድርጅት ከተመሠረተበት 1990 ዓ.ም ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 28 ዓመታት በወጣቶች ልማት፣ በሥነ-ተዋልዶ ጤና፣ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሰውን ጾታዊ ጥቃት በመከላከል፣ በአካባቢ ጥበቃና የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭትና በሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች ዙሪያ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ክልሎችና በአዲስ አበባ መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ለዚህም ተግባሩ ድርጅታችን ላበረከተው የማኅበረሰብ አቀፍ ጉልህ አስተዋኦ ከሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር፣ ከኦሮምያ ክልልና ከኢፊዲሪ መንግስት የሠርትፍኬት፣ የዋንጫ፣ የቦታና የመኪና ሽልማቶችን ያገኘ አንጋፋ ድርጅት ነው፡፡
ድርጅታችን ጣምራ ለማህበራዊ ልማት ድርጅት በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያ ክልል እየተገበረ ለሚገኘው ፕሮጀክቶች የሚውል የህትመት አገልግሎት የሚሰጡንን ድርጅቶች ለማወዳደር ጨረታ ያወጣን ሲሆን ዝርዝር የጨረታ ሃሳቡን እና የሚፈለገውን የህትመት አይነት ዝርዝር የያዘውን ዶክመንት የማይመለስ 200 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነድ በመግዛት ጨረታውን መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን ተጫራች ድርጅቶች ተወካይ መላክ የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
- አድራሻ - ከጃክሮስ ወደ ሳህሊተ ምህረት ቤተክርቲያን በሚወስደው መንገድ አቢሲኒያ ባንክ ጀርባ እንገኛለን
- ለበለጠ መረጃ - 0982024874 ይደውሉ፡፡
Deadline – August 20/2026
Tender details
- Deadline: 2026-08-20
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-08-20 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tamra Economic Development Organization
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: 2merkato.com (Aug 19, 2026)
- Posted at: 2026-08-19T10:11:24.000Z