Textile, Garments and Uniforms
በየካ ክ/ከተማ እንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ የተለያዩ እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019
በየካ ክ/ከተማ እንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ የሚከተሉትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1. የሠራተኞች ደንብ ልብስ
- ሎት 2. የደንብ ልብስ ስፌት
- ሎት 3. ልዩ ልዩ የፅዳት ዕቃዎች ግዥ
- ሎት 4. አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 5. ቋሚ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 6. የህክምና መድሀኒቶች እና ሪኤጀንቶች ግዥ
- ሎት 7. የተለያዩ ጥገና ስራዎች
- ሎት 8. የህትመት ስራዎች
- ሎት 9. ለህንጻ፣ ለቁሳቁስና ለተገጣጣሚዎች ግዥ
- ሎት 10. የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ጥገና ሥራዎች
በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች በሙሉ የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባችኋል።
1. ተጫራቾች የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፍቃድና የፌደራል ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት ዝርዝር መኖራቸውን ማረጋገጫ ደብዳቤ፣ የቫት ተመዝጋቢና ታክስ ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል።
2. ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ በየሎቱ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከጤና ጣቢያው ፋይናንስ ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
3. ለጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/
- ሎት 1. የሠራተኞች ደንብ ልብስ ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 2. የደንብ ልብስ ስፌት ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 3. ልዩ ልዩ የፅዳት እቃዎች ግዥ ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 4. አላቂ የቢሮ እቃዎች ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 5. ቋሚ የቢሮ እቃዎች ብር 10,000.00(አሥር ሺህ ብር)
- ሎት 6. የህክምና መገልገያ ሪኤጀንቶች እና መድሀኒቶች ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 7. የተለያዩ ጥገና ስራዎች ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 8. የህትመት ስራዎች ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር)
- ሎት 9. ለህንፃ ፣ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች ግዥ 3,000.00(ሦስት ሺህ ብር)
- ሎት 10. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ስራዎች ብር 5,000.00(አምስት ሺህ ብር)
ከኦርጅናል ጨረታ ሰነዳችሁ ጋር በፖስታ ውስጥ ተያይዞ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል።
4. ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ እንደተመለከተው መሠረት ከነቫቱ በማሰብ በፖስታ በማሸግ ማህተም ባረፈበት ኦርጂናል እና ኮፒ እሽግ ለያይቶ በማዘጋጀት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል። ኮፒ የሌለው ኦርጅናል ሰነድ ውድቅ ይሆናል።
5. የጨረታው ውጤት እንደታወቀ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒኦ ማስያዝ አለበት።
6. ጨረታው በአየር ላይ የሚውለው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሲሆን በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ይታሸጋል። ጨረታው የሚከፈተው በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በፋይናንስ ክፍል ይከፈታል።
7. የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን እቃ በራሳቸው ትራንስፖርት አጓጉዘው ጤና ጣቢያው ድረስ በማምጣት ገቢ ማድረግ አለባቸው።
8. ተጫራቾች በሌላው ዋጋ ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
9. ተጫራቾች ከጨረታ መክፈቻ ቀን በፊት ባሉት የስራ ቀናት ውስጥ ለሚወዳደሩበት እቃ ናሙና ለሚቀርብባቸው በያይነቱ ናሙና ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው። ናሙና ያልቀረበበት እቃ ዋጋ በሰነዱ ላይ ቢሞሉም ተቀባይነት የለውም።
10. ሎት 7 እና 10 ላይ የምትወዳደሩ ለጥገና የሚያስፈልገው እቃ በተወዳዳሪ የሚሸፈን ይሆናል።
11. ለአነስተኛ እና ጥቃቅን ተወዳዳሪዎች የተደራጃችሁበትን ዘርፍ የሚገልፅ የድጋፍ ደብዳቤ ማምጣት ይኖርባቸዋል።
12. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻችን፡-በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 03 ልዩ ስሙ ቤላ ወይም ጣሊያን
ኤምባሲ ጎን የሚገኝ ሲሆን
ለበለጠ መረጃ፤ እንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ ስልክ ቁጥር 09 13 60 56 32 ፣ 09 13 66 67 47 ወይም 09 91 14 08 79
በየካ ክ/ከተማ እንጦጦ ቁጥር አንድ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-08-31
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00
- Bid opening: 2026-08-31 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Entoto No.1 Health Post
- Buyer address: ልዩ ስሙ ቤላ ወይም ጣሊያን ኤምባሲ ጎን
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: በየሎቱ 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 19, 2026)
- Posted at: 2026-08-19T11:20:36.000Z