Office Machines and Computers

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር የፎቶ ኮፒ፣ እስካነር እና ኘሪንተር ጥገና አገልግሎት ግዥን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር EAC 039/2018

1. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማህበር የፎቶ ኮፒ፣እስካነር እና ኘሪንተር ጥገና አገልግሎት ግዥን በግልጽ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7፡30 -11፡00 ድረስ “ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ” ጉርድ ሾላ ሴንቸሪ ሞል ፊት ለፊት ወይም ላሜ ዴያሪ ጀርባ ከኤልፎር አግሮ ኢንዱስትሪ አጠገብ በሚገኘው የኢትዮ አግሪ ሴፍት ሕንጻ ላይ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 106 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 ብር /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው፣ የታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና የቫት ምዝገባ ሰርተፍኬት ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት

  • አንድ ዋና /Original/ የጨረታ ሰነድ ለብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ታሽጐ
  • አንድ ቅጂ /Copy/ የጨረታ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ ታሽጐ እንዲሁም፣
  • ሁሉም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ውስጥ ተካቶ የታሸገ መሆን አለበት።
  • በዋናውና በቅጂው መካከል ልዩነት ቢፈጠር ዋናው ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ የተሰረዘ ሰነድ በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች የፎቶ ኮፒ፣እስካነር እና ፕሪንተር ጥገና አገልግሎት ግዥን የሚያቀርቡበትን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የጠቅላላ ዋጋ 2% /ሁለት ከመቶ/ የባንክ ክፍያ ማዘዣ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ (Unconditional) ባንክ ጋራንቲ ለኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ቀን ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 208 ሲሆን፣ ጨረታውን የመክፈቻ ቀን ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ 4:45 ላይ ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 106 ይሆናል።

6. ከላይ የተገለጸውን መመሪያ ባልተከተሉ ተጫራቾች ላይ ወዲያውኑ ከጨረታው የሚሠረዝ መሆኑን እንገልጻለን።

7. ተጫራቾች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0116 676 204 ፋክስ ቁጥር 0116 732 006 መጠቀም ይችላሉ።

8. ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማ ጨረታውን በመሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ኢትዮ አግሪ ሴፍት ሃላ.የተ.የግ.ማኅበር


Tender details

  • Deadline: 2026-08-26
  • Bid closing time: 10:30
  • Bid opening: 2026-08-26 10:45
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethio Agri-CEFT Pvt.Ltd.Co.
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 19, 2026)
  • Posted at: 2026-08-19T15:46:28.000Z
← Back to all tenders