Vehicle

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉል የሰራተኞች መኪና ሰርቪስ ኪራይ ግዥ እና የጭነት አገልግሎት ኪራይ ግዥ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉል

  •  በሎት 1፡- የሰራተኞች መኪና ሰርቪስ ኪራይ ግዥ፣
  • በሎት 2፡- የጭነት አገልግሎት ኪራይ ግዥ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም

በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1. ተጫራቾች በሚጠይቀው ዘርፍ የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚገልጽ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉ(tin no) ያላቸዉ፣
  3. የዘመኑን የቴክኒክ ምርመራ አልፎ ቦሎ ያለው።
  4. የተሟላ የመድን ሽፋን ዋስትና ያለዉ።
  5. የባለቤትነት ሊብሬ ማቅረብ የሚችሉ።
  6. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፣
  7. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ከግብር ዕዳ ነፃ ስለመሆናቸው ከገቢዎች መ/ቤት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር፣ ሎት 1፡- የሰራተኞች መኪና ሰርቪስ ኪራይ ግዥ ብር 50,000 ብር /ሃምሳ ሺህ ብር/፣ ሎት 2፡- የጭነት አገልግሎት ኪራይ ግዥ ብር 50,000 ብር /ሃምሳ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፤ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  9. ተጫራቾች ስለጨረታዉ ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘዉን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከመምሪያዉ የግዥና ንብረት አስ/ር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 100 መግዛት ይችላሉ።
  10. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሃሳብ ዋናና ኮፒ በማለት ተፈርሞበት በጥንቃቄ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቂያዉ ከተመለከተዉ የጊዜ ገደብ በፊት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ፣ የግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 100 ለጨረታው በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ገቢ መደረግ አለበት።
  11.  ጨረታዉ ማስታወቂያ በወጣዉ 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ይሆናል።
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
  13.  ሁለቱም ጨረታ ፡- ማለትም ሎት 1 እና ሎት 2 የቫት ተመዝጋቢ ባይሆኑም መሳተፍ ይችላሉ።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0471355629

የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-05
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-05 15:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: Benchi Sheko Zone Finance Bureau
  • Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 20, 2026)
  • Posted at: 2026-08-20T08:35:31.000Z
← Back to all tenders