Labour Outsourcing Services

የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ የእህል ዘሮች አጨዳ እና ከማሳ ወደ አውድማ የማጓጓዝ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር OSE/ NCB/005/2019

የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ የእህል ዘሮች አጨዳ እና ከማሳ ወደ አውድማ የማጓጓዝ ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

ስለሆነም አስፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች፡-

1. የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት

2. የዘመኑን የታደሰ ንግድ ፈቃድ

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት

4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO)

5. የአቅራቢነት ማስረጃ (Suppliers List)

6. የሚፈለግባቸውን የመንግሥት ግብር ስለመወጣታቸው የሚገልጽ ማስረጃ፣ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።

ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን በመግዛት በ16ኛው የሥራ ቀን ጨረታው የሚዘጋና የሚከፈት ይሆናል። የጨረታ ሰነድ መግዣ ዋጋ ብር 300 (ሶስት መቶ) መሆኑን እየገለጽን ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውን በፖስታ በማሸግ በተጠቀሱት ቀናት ከጠዋቱ 2:30-8፡00 ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን።

የጨረታ ሳጥኑ ከላይ በተጠቀሱት ቀናት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢንተርፕራይዙ ዋና መ/ቤት ጎተራ አጎና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ህንፃ /Baleker Tower/ 4ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 402 ይከፈታል።

ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የሠሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢንተርፕራይዙ የሥራ ሰዓት፧

ከሰኞ-አርብ ጠዋት ከ2፡30-6፡30 ከሰዓት በኃላ ከ7፡30-11፡30 ነው።

ለበለጠ ማብራሪያ፡- ስ.ቁ 011 416 0309 / 011 466 2527 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የኦሮሚያ ምርጥ ዘር ኢንተርፕራይዝ


Tender details

  • Deadline: 2026-10-05
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን በመግዛት በ16ኛው የሥራ ቀን በ8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-10-05 14:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ሰነዱን በመግዛት በ16ኛው የሥራ ቀን በ8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Oromia Seed Enterprise
  • Buyer address: ጎተራ አጎና ሠራዊት ሲኒማ አጠገብ ባለኬር ህንፃ /Baleker Tower 4ኛ ፎቅ ላይ
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 19, 2026)
  • Posted at: 2026-09-19T08:22:19.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders