Office Machines and Accessories

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የሀብሩ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ለሀብሩ ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች የተለያዩ ዕቃዎችን እና አስተዳደር ጽ/ቤት ለሚሰራው አጥር ግንባታ ስራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል

Description

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2019

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የሀብሩ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ለሀብሩ ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት ሎት1 የቋሚ የቢሮ እቃ፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃ፤ ኤሌክትሮኒክስ፣ የመኪና እቃ መለዋወጫ ግዥ በዘርፉ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው አቅራቢዎች እንዲሁም ሎት2 ለሀ/ወ/ጤና እና አስተዳደር ጽ/ቤት ለሚሰራው አጥር ግንባታ ስራ ለማሰራት ደረጃ 6 እና ከዚያ በላይ ፈቃድ ያላቸውን GC/BC በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆን ይጋብዛል።

1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው በተጠየቁት የግዥ አይነትና ዘርፍ የንግድ ፍቃድ ማቅርብ የሚችሉ

2 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው

3. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

4. በውሉ መሰረት ያሸነፈበትን እቃ ግዥ ኦርጅናል እቃዎች ማቅረብ የሚችል።

5. ማስታወቂያ አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ለሴ/መቤቶች በመደበኛ በጀት የቋሚ የቢሮ እቃ የጽህፈት መሳሪያ፣ የጽዳት እቃ የኤሌክትሮኒክስ የመኪና እቃ መለዋወጫ ግዥ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት አጥር ግንባታ ስራ በ21 ቀናት እስከ 11፡30 የስራ ቀን ድረስ ብቻ ነው።

6. የጨረታውን ማስከበሪያ ለቋሚ የቢሮ እቃ 20000/ሀያ ሺህ ብር/ ፣ ለጽህፈት መሳሪያ 40000/አርባ ሺህ ብር/ ለጽዳት እቃ 9000/ዘጠኝ ሺህ ብር/ ለኤሌክትሮኒክስ 15000/አስራ አምስት ሺህ ብር/ለመኪና እቃ ለመለዋወጫ 30000/ሰላሳ ሺህ ብር/ ፤ለአጥር ግንባታ ስራ 50000/ሀምሳ ሺህ ብር/ CPO ያስያዙ ወይም ገንዘቡን አስቀድሞ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ኮፒ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ያቀርባሉ።

7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድና መመሪያ ለእያንዳንዱ ለተጠየቀ ግዥ ሰነድ በማይመለስ ብር 150.00 /አንድ መቶ ሀምሳ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ዝርዝር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት ጨረታው አየር ላይ ከሚቆይበት እስከ መጨረሻ ቀን እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 08 በመገኘት መግዛት ይችላሉ።

8. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት ለሴ/መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት የቋሚ የቢሮ እቃ የጽህፈት መሳሪያ ለጽዳት እቃ፣የኤሌክትሮኒክስ የመኪና እቃ መለዋወጫ ግዥ በ16ኛው ቀን አጥር ግንባታ ስራ በ21ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 08 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. የጨረታ ሳጥኑ በ4፡00 ሰዓት ይታሸጋል የጨረታ ሰነድ ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

10. የጨረታ ሳጥን የሚከፈትበት ቦታ ግዥ ንብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 08 ለ-/ወ/ሴ/መ/ቤቶች በመደበኛ በጀት የቋሚ የቢሮ እቃ የጽህፈት መሳሪያ የጽዳት እቃ የኤሌክትሮኒክስ ለመኪና እቃ ለመለዋወጫ ግዥ በ16ኛው ቀን ለአጥር ግንባታ ስራ በ21ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች እራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል ጨረታው የሚከፈትበት እለት የስራ ቀን ካልሆነ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል።

11. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ከሆኑ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርብዎታል።

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 08 ድረስ በአካል በመገኘት ማግኘት ይችላሉ።

14. አሸናፊው የሚለየው በሎት ድምር ውጤት መሰረት ይሆናል።

በሰሜን ወሎ ዞን የሀብሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-09
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid opening: 2026-09-09 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: North Wollo Zone Habru Woreda F/E/D/Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 150.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 20, 2026)
  • Posted at: 2026-08-20T10:22:50.000Z
← Back to all tenders