Textile, Garment and Leather

የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የመ/ደ/ት/ቤት በ2019ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግዢ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡-0001/2019

የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የመ/ደ/ት/ቤት በ2019ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች ማለትም ፡-

  • ሎት-1- የደንብ ልብሶች
  • ሎት-2- አላቂ የቢሮ እቃዎች
  • ሎት-3 ልዩልዩ አላቂ የህክምና ዕቃዎች
  • ሎት-4- አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
  • ሎት-5- አላቂ የፅዳት ዕቃዎች
  • ሎት-6 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
  • ሎት-7 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ተጫራቾች፡-

1. በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች በዘርፉ ወይም በመስኩ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።

3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በአዲስ አበባ ማረሚያ የመ/ደ/ት/ቤት ስም በባንክ ሲፒኦ (CPO) ለእያንዳንዱ ለሚሳተፉበት ሎት ማስያዝ ግዴታ አለበት።

6. ይህ ጨረታ ጸንቶ የሚቆየው ለ60 ቀን ብቻ ነው።

7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአዲስ አበባ ማረሚያ የመ/ደ/ት/ቤት(በቃሊቲ ማረሚያ ቤት) በፋይናንስ ቢሮ ቁ.3 ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከትምህርት ቤቱ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረብያ ቦታ በግልጽ በመሙላት በመጨረሻ ቦታ ላይ ስም ፣ ፊርማና ህጋዊ ማህተም በማኖር በታሸገ ኤንቨሎፕ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በማሸግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘውትር በስራ ሰዓት ከ2፡30-11፡30 ዋጋቸውን በመሙላት በተጠቀሰው የስራ ሰዓት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

9. ለጨረታ ማስከበርያ የሚሆን በየሎቱ ከታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

1

ሎት1-የደንብ ልብስ

40,000

2

ሎት2-አላቂ የቢሮ ዕቃዎች

22,000

3

ሎት3-አላቂ የት/ ዕቃዎች

1,000

4

ሎት4-የላብራቶሪ ዕቃዎች

20,000

5

ሎት5-የፅዳት ዕቃዎች

60,000

6

ሎት6-ልዩ ልዩ መሳሪያዎች

20,000

7

ሎት7-ቋሚ እቃዎች

40,000

10. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ሊዘጋ አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

11. ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ 10% ባሸነፉበት ዕቃ መጠን መሰረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርቦታል።

12. ጨረታውን ለማባዛት የሚሞክር ከጨረታው ውጪ እንደሚሆንና የጨረታውን ማስከበሪያ CPO እንደሚወረስባቸው ማወቅ አለባቸው።

13. በጥቃቅን እና አነስተኛ ለተደራጁ ተጫራቾች ለሚያመርቱት ምርት ብቻ ከክፍያ ነፃ ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ በማፃፍ እና ለማያመርቱት ምርት /ዕቃ/እንደማንኛውም ተጫራች ሰነዱን በመግዛት እና በየሎቱ የተቀመጠውን የጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ መሳተፍ ይችላሉ።

14. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በወጣ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 በትምህርት ቤቱ በፋይናንስ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 03 ይከፈታል።

15. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

16. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-59-15-24-03 / 09 59-15-25-68

ለበለጠ መረጃ ፡- አድራሻ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 7 አዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ

የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት የመ/ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-01 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቅያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Prison Primary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 20, 2026)
  • Posted at: 2026-08-20T11:03:05.000Z
← Back to all tenders