Textile, Garment and Leather

የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 001/2019

የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ተጫራቾች ፡-

1. በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ተመዝግበው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እና ቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. ተጫራቾች በዘርፉ ወይም በመስኩ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው።

3. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

4. ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

5. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ሁ/ደ/ት/ቤት ስም በባንክ ሲፒኦ (CPO) ለእያንዳንዱ ለሚሳተፍበት ሎት ማስያዝ ግዴታ አለበት።

6. ይህ ጨረታ ጸንቶ የሚቆየው ለ60 ቀን ብቻ ነው።

7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በአዲስ አበባ ማረሚያ የሁ/ደ/ት/ቤት (በቃሊቲ ማረሚያ ቤት) በፋይናንስ ቢሮ ቁ.3 ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ከትምህርት ቤቱ ግዢ እና ንብረት አስተዳደር የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልጽ በመሙላት በመጨረሻው ቦታ ላይ ስም ፣ ፊርማና ህጋዊ ማህተም በማኖር ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘውትር በስራ ሰዓት ከ2፡30-11፡30 ዋጋቸውን በመሙላት በተጠቀሰው የስራ ሰዓት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

9. ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በየሎቱ ከታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

1

ሎት1-

6211 ደንብ ልብስ

ብር 30,000.00

2

ሎት2-

6212 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች

ብር 15,000.00

3

ሎት3-

6214 አላቂ የህክምና ዕቃዎች

ብር 6,000.00

4

ሎት4-

6215 አላቂ የት/ ዕቃዎች

ብር 30,000.00

5

ሎት5-

6218 የፅዳት ዕቃዎች

ብር 40,000.00

6

ሎት6-

6219 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች

ብር 10,000.00

7

ሎት7-

6313 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች

ብር 40,000.00

10. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ሊዘጋ አንድ ቀን እስኪቀረው ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

11. ጨረታውን አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ 10% ባሸነፉበት ዕቃ መጠን መሰረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርቦታል።

12. ጨረታውን ለማባዛት የሚሞክር ከጨረታው ውጪ እንደሚሆንና የጨረታውን ማስከበሪያ CPO እንደሚወረስባቸው ማወቅ አለባቸው።

13. በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራዝ የተደራጁ አምራች ድርጅቶች የዋስትና ደብዳቤ ካደራጃቸው አካል ማቅረብ ይኖርባቸዋል። አምራች ካልሆኑ ደግሞ አምራች ከሆነው የሀገር ውስጥ ድርጅት ትስስር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

14. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በአየር ላይ ይቆይና በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ይዘጋና ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

15. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው።

16. ስርዝ ድልዝ ወይም በፍሉድ የተስተካከለ ማንኛውም ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።

አድራሻ ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ክራውን ሆቴል ፊት ለፊት ፌዴራል ማረሚያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ

አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ስልክ ቁጥር፡- 09 88 36 49 45 / 09 88 31 60 45

የአዲስ አበባ ማረሚያ ቤት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በአየር ላይ ይቆይና በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-01 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር ተከታታይ 10 የስራ ቀናት በአየር ላይ ይቆይና በአስራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Prison Primary & Secondary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 20, 2026)
  • Posted at: 2026-08-20T11:06:06.000Z
← Back to all tenders