Textile, Garments and Uniforms

በየካ ክ/ከ የወ01 ጤና ጣቢያ የደንብ ልብሶች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ህትመቶች፣ የጽዳት እቃዎች፣ የጥገና እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ቋሚ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 001/19

በየካ ክ/ከ የወ01 ጤና ጣቢያ በ2019 በጀት አመት በመንግስት ከተመደበለት ትሬዠሪና የውስጥ ገቢ መደበኛ በጀት በ1ኛ ዙር ብሄራዊ ግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን የደንብ ልብሶች፣ የጽህፈት መሳሪያዎች ህትመቶች የጽዳት እቃዎች የጥገና እቃዎች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ቋሚ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ በባንክ በተረጋገጠ /ሲ.ፒ.ኦ/

  • ሎት 6211 (70,000.00)ሰባ ሺህ ብር
  • ሎት 6212 (85,000.00) ሰማንያ አምስት ሺህ
  • ሎት 6213 (45,000.00)አርባ አምስት ሺህ
  • ሎት 6218(70,000.00)ሰባ ሺህ ብር 
  • ሎት 6244 (45,000.00)አርባ አምስት ሺህ
  • ሎት 6313 (550,000.00) አምስት መቶ ሃምሳ ሺህ
  • ሎት 6314 (35,000.00)ሰላሳ አምስት ሺህ ብቻ በማሰራት ዋናውን/ኦርጅናል ከሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች ፡-

2. የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፤ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

3. ከፋ/ኢ/ል/ ሚኒስቴር በእቃ ግዥ አቅራቢነት ለተወዳዳሪነት የተፈቀደበት የምዝገባ ማስረጃቸውን ማቅረብ አለባቸው።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር /ብቻ በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን ድረስ ከተቋሙ ግዥ ክፍል መውሰድ የምትችሉ ሲሆን የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚጫረቱበትን ዋጋ ከነ ቫት በመሙላት እና ስም ! ፊርማና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም በማድረግ ዋናውንና ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ በተቋሙ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

5. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን 11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በይፋ ይከፈታል።

6. እቃዎቹ በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት መቅረብ አለባቸው። ኤክስፓየርድ ዴት ለሚያስፈልጋቸው የተመረቱባቸውና ኤክስፓየርድ ጊዜያቸው በግልጽ የሚታይ መሆን አለባቸው። የአገልግሎት ጊዜያቸው ቢያንስ አንድ አመት እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው።

7. ዋጋችሁን ስትሞሉ የምትሞሉትን ዋጋ ጠቅላላ ድምር እንድታስቀምጡ።

8. ውል በሚገቡበት ጊዜ አጠቃላይ ያሸነፉትን ዋጋ 10% ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባችኋል።

8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ፡- ፈረንሳይ ወደ አርባ አንድ እየሱስ በሚያስገባው መንገድ ገባ ብሎ ከወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት አጠገብ።

ለበለጠ መረጃ ፡- ስልክ ቁጥር 011 154 9680
የካ ክ/ከ የፈረንሳይ አካባቢ
ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን 11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-02 12:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yeka Sub City Woreda 01 Health Post
  • Buyer address: ፈረንሳይ ወደ አርባ አንድ እየሱስ በሚያስገባው መንገድ ገባ ብሎ ከወረዳ 01 አስተዳደር ጽ/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
  • Posted at: 2026-08-21T09:54:03.000Z
← Back to all tenders