Catering and Cafeteria Services
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2019 በጀት አመት የህሙማን የሚቀርብ የበሰለ የምግብ አቅርቦት አውት ሶርስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት እና መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል በ2019 በጀት አመት የህሙማን የሚቀርብ የበሰለ የምግብ አቅርቦት አውት ሶርስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት እና መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሱ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነበር ያላቸው ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የዘመኑን ግብር የከፈለ የግብር ከፋያ መለያ ቁጥር ያለው ጨረታው ለማሸነፍ የሠጠው አመታዊ ዋጋ ከ200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር / እና በላይ ከሆነ ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ አለበት።
3. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦርጅናሉንና ኮፒ በጥንቃቄ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
4. ዝርዝር መግለጫ /እስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ:: የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር / ብቻ በመያዝ በአጣዬ ዲስትሪክት ሆስፒታል ግዥ ፋይናስ ገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ።
5.ተጫራቾች ጨረታ ከመክፈቱ በፊት የተወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ የጨረታ ማስከበሪያ 1% እና ካሸነፈ በኋላ ያሸነፈበትን ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ በጥሬ ገንዘብ ሆስፒታል ገንዘብ ቤት ድረስ ቀርበው ማስያዝ አለባቸው።
6. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም በአንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቢሮ ግዥ ፋይናንስ ቁጥር 44 የስራ ሂደት በዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ ማስገባት ትችላላችሁ፡፡ ጨረታዉ 4፡00 ይታሸጋል፤ ወዲያውኑ 4፡00 ሰዓት ላይ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥ ፋ/ን/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት በስልክ ቁጥር በሞባይል 0913005480 /0912920272 /0913023571 ቁጥር በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
7. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ፀንቶ ለ20 /ሃያ/ ቀን ይቆያል።
8. የመክፈቻው ዕለት በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
9. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፁትን ሁኔታዎች ቢኖሩ በግዥ መመሪያው ተግባር መሆን አለባቸው።
10. ለወሰዱት የተጫራቾች መመሪያ ለእያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅታችሁን ማህተም ማድረግ እና አብረው ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
11. ጨረታውን የምናወዳድረው በጥቅል ወይም በነጠላ ሊሆን ይችላል።
12. የተደራጁ ከሆኑ ካደራጃቸው መ/ቤት ህጋዊ የዋስትና ደብዳቤ ማፃፍ ይጠበቃባቸዋል።
13. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. ግብር የከፈሉበት ከገቢዎች ፅ/ቤት የሚሰጥ ክሪላንስ አብረው ማስያዝ አለባቸው።
15. ስርዝ ድልዝ ቢኖር ፓራፍ መደረግ አለበት።
16.እያንዳንዱ ገፅ ላይ የድርጅታቸው ማህተም መደረግ አለበት።
የሰ/ሸዋ ዞን የአጣዬ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
Tender details
- Deadline: 2026-09-05
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00
- Bid opening: 2026-09-05 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00
- Region: Amhara
- Publishing entity: Ataye Primary Hospital
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
- Posted at: 2026-08-21T10:45:16.000Z