Sport Materials and Equipment

ወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ በ2019 በጀት ለስፖርት ክለብ የተለያዩ የውድድርና የልምምድ ትጥቆችንና ቁሳቁሶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የማስታወቂያ ቁጥር ወድስክ 09/2018 ዓ.ም

ወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ በ2019 በጀት ለስፖርት ክለብ የተለያዩ የውድድርና የልምምድ ትጥቆችንና ቁሳቁሶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች አሟልተው መቅረብ ያለባቸው መስፈርቶችና ግዴታዎች፡-

1. በግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በሚወዳደሩበት ንግድ ዘርፍ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

3. ተጫራቾች ሁሉንም ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከታተመበት ቀን አንስቶ በተከታታይ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ዘውትር በክለቡ ሥራ ሰዓት ወላይታ ሶዶ ስታድዬም በምገኘው ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች ለተሸናፊዎች ከጨረታ ግምገማ በኋላ የሚመለስ የጨረታ ዋስትና ለመወዳደር ባቀረቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ በማስላት 2% በባንክ የተመሠከረለት በወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ ስም የተሠራውን ሲፒኦ ከጨረታ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የውል ማስከበሪያ ዋስትና አሸናፊነቱ ከተረጋገጠበት/ ከተገለፀበት ቀን አንስቶ ባሉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ውስጥ በአሸነፉበት ዋጋ መጠን ተሰልቶ 5% በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሠከረ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት። ለማስያዝ ፈቃደኛ ካልሆነ ለጨረታው ዋስትና ያስያዘው ብር በሙሉ ለክለቡ ውርስ ይደረጋል።

6. አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብና አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ አላቀርብም ማለት የጨረታ ዋስትናውን ያስቀጣል።

7. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያውንና የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን ዋናውንና ፎቶኮፒውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በወላይታ ሶዶ ስታዲዬም በሚገኘው ጽ/ቤት በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ፖስታ በጨረታ ሣጥን የሚገባው የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ይፋ ከሆነበት ቀን አንስቶ ቅዳሜና እሁድ ጨምሮ በተከታታይ እስከ 10ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ድረስ ገቢ ሆኖ ልክ በዕለቱ በ8፡30 ሰዓት ጨረታ ሣጥን ተዘግቶ /ታሽጎ/ ፈቃደኛ የሆኑ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ተወካዮችና ታዛቢዎች በተገኙበት ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት በይፋ ይከፈታል። አስረኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም ሕጋዊ በዓል ቀናት ከዋለ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ወላይታ ሶዶ በሚገኘው ጽ/ቤት ይከፈታል።

8. አንድ ተጫራች የሚያሠራው ሲፒኦ በሕጋዊ ባለመብት ወይም ድርጅት ስም የተሠራ መሆን አለበት።

9. ተጫራቾች በጨረታ የሚወዳደሩባቸውን የሎት አይነቶች ለይተው መጻፍ አለባቸው እንዲሁም ለየብቻ በሎት ዓይነቶች መወዳደር ይችላሉ።

10. ክለቡ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት 20-30% እንደአስፈላጊነቱ በመጨመር ወይም በመቀነስ መግዛት ይችላል።

11. የጨረታ ሰነድ ስርዝ ድልዝ ካለው ወይም ግልፅ ሆኖ ካልታየ ተቀባይነት አይኖረውም።

12. ለጨረታዉ አሸናፊ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ከ3-5 ባሉት ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ዕቃዉን ማቅረብ አለበት።

13. ክለቡ በጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09-27-04-91-59 ወይም 046-180-4343 / 09-12-40-29-82 መጠቀም ይችላሉ!

የወላይታ ድቻ ስፖርት ክለብ


Tender details

  • Deadline: 2026-08-31
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ይፋ ከሆነበት ቀን አንስቶ ቅዳሜና እሁድ ጨምሮ በተከታታይ እስከ 10ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-31 15:00
  • Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ይፋ ከሆነበት ቀን አንስቶ ቅዳሜና እሁድ ጨምሮ በተከታታይ እስከ 10ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 9፡00 ሰዓት
  • Region: South Ethiopia Regional State
  • Publishing entity: Wolayita Dicha Sport Club
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 400.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
  • Posted at: 2026-08-21T10:53:14.000Z
← Back to all tenders