Vehicle
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዓለም ገና መ/ጥ/ዲስትሪክት 25 ሰው መጫን የሚችል የሠራተኞች ሰርቪስ (አውቶብሶች) በቁጥር 6 (ስድስት) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል
Description
አስቸኳይ የጨረታ ማስታወቂያ ጨ-47-2018
የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዓለምገና መ/ጥ/ዲስትሪክት ስር ለሚገኙ ፕሮጀክቶችየሚሆን 25 ሰው መጫን የሚችል የሠራተኞች ሰርቪስ (አውቶብሶች) በቁጥር 6 (ስድስት)በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
ስለሆነም በዚህ ጨረታ ስመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች ያለውን ሁኔታ በማሟላት መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ያሳውቃል።
|
ተ/ቁ |
መስፈርት |
ዝቅተኛ መስፈርት |
|
1 |
የተሽከርካሪ ዓይነት |
አውቶብስ/ኮስትር/ ዓይነት ወይም ተመጣጣኝ |
|
2 |
የተሳፋሪው መቀመጫ አቅም |
ቢያንስ 25 |
|
3 |
የተሽከርካሪ ሁኔታ |
ደህንነቱ የተጠበቀ ንፁህና ለመንገድ ጉዞ ተስማሚ |
|
4 |
የምርት (የስሪት) ዘመን |
እ.ኤ.አ 2015 እና ከዚያ በላይ |
|
5 |
አየር ማቀዝቀዣ |
ግዴታ /አማራጭ/ |
|
6 |
የመቀመጫ ቀበቶ |
በአምራቹ የተገጠመ ከሆነ ግዴታ ነው |
|
7 |
ምዝገባ |
የሚያገለግል የኢትዮጵያ ተሽከርካሪ ምዝገባ |
|
8 |
የመንገድ ብቃት |
የሚያገለግል የተሽከርካሪ ምርመራ/ማረጋገጫ/ |
|
9 |
ኢንሹራንስ |
የሚያገለግል የኢንሹራንስ ሽፋን |
|
10 |
አሽከርካሪ |
ብቃት ያለውና ተገቢውን የመንጃ ፍቃድ ያለው |
- ተጫራቾች በሥራ ዘርፍ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማስረጃ ያላቸው እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሠርተፍኬት ማስረጃ ከጨረታው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት አለምገና በሚገኘው የመ/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ) ከፍለው የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ከግዥ አቅርቦትና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ መውሰድ ይችላል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱትን ተሽከርካሪ በመግለፅ ከተዛማጅ ማስረጃዎቻቸው ጋርሁሉንም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን በግዥ አቅርቦትና ንብረት አስተዳደር ቡድን ገቢ የሚያደርጉበት የመጨረሻ ቀን 30/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ብቻ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 የባንክ ዋስትና ወይም CPO ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት።
- የጨረታ ሳጥኑ 30/12/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 በዓለምገና መ/ጥ/ዲስትሪክት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- ተጫራቾች አላስፈላጊ ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገቡበት ቅፅ ሞልተውና ፈርመው ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር ለማቅረብ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው።
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- አውቶብሱ ተቀያሪ ጎማ ፣እሳት ማጥፊያ፣የመጀመሪያ ዕርዳታ መስጫ ኪት እና የአደጋ ጊዜ መውጫ ሊያሟላ ይገባል።
ለበለጠ መረጃ
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የአለምገና መ/ጥ/ዲስትሪክት
ስልክ ቁጥር 011-387-10-28/0912117911
አድራሻ፡- ዓለምገና ቀበሌ 02 ከአዲስ አበባ ወደ ሰበታ መውጫ
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የአለምገና መ/ጥ/ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-09-05
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-05 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Roads Authority Alemgena Road Maintenance District
- Buyer address: ዓለምገና ቀበሌ 02 ከአዲስ አበባ ወደ ሰበታ መውጫ በስተቀኝ በኩል
- Bid bond: 20,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
- Posted at: 2026-08-21T10:56:39.000Z