Vehicle

የገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ማሽነሪዎች (ማለትም ዶዘር፣ ግሬደር፣ ኤክስካቫተር፣ ሎደር፣ ገልባጭ፣ ሩሎ፣ ባኮሎደር ፒካፕ እና አውቶሞቢል መኪናዎችን) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል

Description

 ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ለክፍለ ከተማው ማዘጋጀ ቤት መሰረተ ልማት ስራ አገልግሎት የሚውሉ ማሸነሪዎች (ማለትም ዶዘር ፤ ግረድር ፤ ኤክስካቫተር፤ ሎደር ፤ ገልባጭ፤ ሩሎ፤ ባኮሎደር ፒካፕ እና አውቶሞቢል መኪናዎችን) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የምታሉ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ።

  • ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የታደሰ እንዲሁም የሚፈለግባችውን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው በቂ ማስረጃ (ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችሉ።
  • ተጫራቾች ዝርዝር የጫረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 2000.00 (ሁለት ሺህ ብር) ወደ ስንቄ አካውንት ቁጥር 10544901611217 ገቢ በማድረግ ከገቢዎች ባለስልጣን በተወከለው ሠራተኛ አማካኝነት ወደ ደረሰኝ በማስቀየር ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ዓርብ (2፡30-1፡30) መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የጫረታ ማስከበሪያ በምያቀርቡት ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረለት CPO ብቻ በገላን ጉዳ ገንዝብ ጽ/ቤት ስም አዘጋጅተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች ሰነዱን ከገዙ በኃላ የምያከራዩቤትን ዋጋ በመጥቀስ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማሸግ በተባለው ቀን ውስጥ ለጫረታው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት 5% ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል ፤ እንዲሁም ተጫራቾች የሚሰጡት ማሽኔሪዎች ዋጋ ቫትን (15%) ያካተተ መሆን አለበት።
  • ተጫራቾች ያሸነፉትን ማሽኔሪዎች መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው ቦታ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች ያሸነፉትን ማሽኔሪዎች አስፈላጊውን ጥራት የተጠየቀውን ሞዴል ማሟላቱ በባለሙያ ሲረጋገጥ ብቻ የምንከራይ ይሆናል።
  • ተጫራቾች የሚያቀርቡት ማሽኔሪዎች ባለቤትነቱ የራሳቸው ወይም በክራይ ከሆነ ሙሉ ውል እና ልብሬ አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  •  የጨረታው ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራት ቀናት የሚሸጥ ሆኖ በ16ኛው ቀን፣ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ቀን 4፡30 የሚከፈት ይሆናል።
  • ከላይ የተገለጸው የመክፈቻ ቀን በዓል ወይንም የሰንበት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በቀጣዩ የስራ ቀን ይሆናል።
  • አድራሻ ገላን ጉዳ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት በተለምዶ አለምገና (ኬንቴሪ ) ዋንጋር ሕንጻ 3ፎቅ ነው።
  • መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጫረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የገላን ጉዳ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-08
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራት ቀናት የሚሸጥ ሆኖ በ16ኛው ቀን፣ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-08 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 የስራት ቀናት የሚሸጥ ሆኖ በ16ኛው ቀን፣ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Gelanguda Sub-City Finance Bureau
  • Bid bond: 100,000.00 ብር
  • Bid document price: 2000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
  • Posted at: 2026-08-21T11:47:12.000Z
← Back to all tenders