Textile, Garment and Leather

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ስር የሚገኘው የዓለም ማያ የመጀመሪያና/መካ/ደ/ት/ቤት በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን አወዳድሮ ግዢ መፈጸም ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ስር የሚገኘው የዓለም ማያ የመጀመሪያና/ መካ/ደ/ት/ቤት በ2019 ዓ.ም የበጀት ዓመት የምንፈልጋቸው ዝርዝር ዕቃዎች

  • ሎት 1 እና 2 የደንብ ልብስ እና ስፌት የጨረታ ማስከበሪያ በብር 10,000
  • ሎት3 ፤5እና 6 አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችና የቢሮ ዕቃዎች እንዲሁም የጽዳት ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር 5,000
  • ሎት 4 ህትመት የጨረታ ማስከበሪያ በብር 3,000
  • ሎት7 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር 8,000
  • ሎት 8 ቋሚ የፈርኒቸር ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ በብር 8,000
  • ሎት 9 የኤሌክትሮኒክስ እድሳትና ጥገና የጨረታ ማስከበሪያ በብር 25,000
  • ሎት 10 የተለያዩ እድሳትና ጥገና የጨረታ ማስከበሪያ በብር 50,000

ብቃት ያላቸው እና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዢ መፈጸም ይፈልጋል

በዚህም መሰረት

1/ በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ንግብር የከፈሉ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድረ ገፅ ላይ አቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡበት የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ተጫራቾች በመንግስት መስሪያ ቤት ግዥ በማንኛውም ጨረታ እንዳይሳተፉ ተብለው እገዳ ያልተጣለባቸው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

2/ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

3/ተጫራቾች ጨረታውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጠበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ በመክፈል በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ስር የሚገኘው የዓለም ማያ የመጀመሪያና/ መካ/ደ/ት/ቤት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

4/ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶችን በሰም በታሸገ ፖስታ /ኤንቨሎፕ/ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 /አስር/ የስራ ቀናት በት/ቤቱ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡

5/ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10 /አስረኛው/ ቀን በ11 /አስራ አንድ / ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ ከጠዋቱ 3፡30/ሶስት ሰዓት ተኩል/በዓለም ማያ የመ/መካ/ደ/ት/ቤት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ የስራ ሰዓት ይከፈታል፡፡

6/ ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባው ሎት1 ፤ 3፤ 4፤ 5፤ 6፤ 7፤ 8 ናሙና /ሳምፕል/ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሳምፕሉን ሲያቀርቡ ግን ዕቃውን የሚገልጽ ሳምፕል መሆን አለበት እንዲሁም በሳምፕሉ ላይ ድርጅቱን የሚገልጽ ምልከት መቀመጥ አለበት። አለበለዚያ ግን ድርጅቱ የማይታወቅ ሳምፕል ውድድር ውስጥ ሊካተት /ሊወዳደር/ አይችልም፡፡

7/ ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች የአንዱን ዋጋ ከነ ቫቱ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል ፡፡

8/ የዘገየ ጨረታ እና በመከፈቻ ሰዓት ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡

9/ አሸናፊ ተጫራቾች ዕቃውን በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

10/ መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማብራሪያ ጥያቄ ካላችሁ አድራሻ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ስር የሚገኘው የዓለም-ማያ የመጀመሪያና/ መካ/ደ/ት/ቤት በርበሬ በረንዳ ፔፕሲ ፋብሪካ አጠገብ

ስልክ ቁጥር ፡ 0112 134 457 / 0112 733 693/92

በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 የዓለም-ማያ የመጀመሪያና/ መካ/ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጠበት እለት ጀምሮ በአስረኛው ቀን በ11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-02 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጠበት እለት ጀምሮ በአስራ አንድኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lideta Sub City Education Bureau Alem Maya Elementary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
  • Posted at: 2026-08-21T11:50:32.000Z
← Back to all tenders