Spare Parts and Car Decoration Materials
የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሰራት ይፈልጋል
Spare Parts and Car Decoration MaterialsCleaning and Janitorial Equipment and ServiceStationery
Dire Dawa
More tags
Office Supplies and ServicesPrinting and PublishingVehicleRentHotel Service ProvisionHospitality, Tour and TravelCatering and Cafeteria ServicesTransportation ServiceWarehousing, Transit and Transport ServiceTour and TravelAmharic2merkatoDire Dawa Administration Urban Development and Construction Bureau
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ድ/ዳ/አስ/ከ/ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ /002/2018
የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ
1. የተለያዩ የተሽከርካሪዎች ጎማ እና ባትሪዎች
2. ለቢሮ መገልገለያ የሚዉል አላቂ የጽህፈት መሳሪያና የጽዳት እቃዎችን
3. የህትመት ስራዎች
4. መኪና ኪራይ, ለሰራተኞች ሰርቪስ እና ለመስክ ስራ የሚያገለግሉ
5. የሆቴል መስተንግዶ አዳራሽና ሪፍሬሽመንት
ከዝህ በታች የተገለጸውን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሰራት ይፈልጋል
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለጹትን መሰፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- በዘርፉ ለ2019 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፣
- የንግድ ዋና ምዝገባ የምስክር ወረቀት የሚያቀርብ፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ / ቫት/ ተመዝጋቢ የሆነ ለዚህም የምስክር ወረቀት የሚያቀርብ ፣
- የታክስ መለያ ቁጥር /ቲን/ የምስክር ወረቀት የሚያቀርብ ሆኖ የሚቻረቱበት የግዥ ዓነት
- የተለያዩ የተሸከርካሪዎች ጎማ እና ባትሪ
- የመኪና ኪራይ( ለሰራተኞች ሰርቪስና ለመስክ ስራ የሚያገለግል)
- የህትመት ስራራዎች፤
- የመስተንግዶ አዳረሽና ሪፍሬሽመንት እንዲሁም
- ለቢሮ መገልገያ የሚዉል አላቂ የጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት እቃዎች ናቸዉ ፣
- የጨረታ ማስከበሪያ ለሁሉም የግዥ አይነቶች በእያአንዳንዳቸዉ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር ብቻ/ በገንዘብ ወይም በሲፒኦ ማቅረብ አለበት
- ከዚህ በላይ የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟላ ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በመልዕክተ ድሬ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ቁጥር 203 ድረስ በአካል በመቅረብ የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛትና መወዳደር ይችላል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በመልዕክተ ድሬ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 / አስራ አምስት / የስራ ቀናት የአየር ላይ ቆይታ በኋላ በ16 ኛው ቀን በቢሮው የግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 203 ከጠዋቱ 3፡00 ላይ የጨረታ ሰነድ መቀበያ ሳጥኑ ተዘግቶ /ታሽጎ/ በዚያኑ እለት ከጠዋቱ 3:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሚውለው ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከዚህ በላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።
- ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ ማብራሪያ የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ቁጥር 203 ወይም በስልክ ቁጥሮች 025 211 1309 / 09 94 01 32 09 / 09 28 21 83 74 ላይ በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል።
Tender details
- Deadline: 2026-08-29
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በመልዕክተ ድሬ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 / አስራ አምስት / የስራ ቀናት የአየር ላይ ቆይታ በኋላ በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00
- Bid opening: 2026-08-29 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በመልዕክተ ድሬ ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 / አስራ አምስት / የስራ ቀናት የአየር ላይ ቆይታ በኋላ በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30
- Region: Dire Dawa
- Publishing entity: Dire Dawa Administration Urban Development and Construction Bureau
- Bid bond: 10,000.00 ብር ለእያንዳንዳቸው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Melekite Dire (Aug 12, 2026)
- Posted at: 2026-08-21T12:33:06.000Z