Sport Materials and Equipment
የቀለም አምባ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2019
የቀለም አምባ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች በሎት የተገለፁትን
- ሎት 1፦ የደንብ ልብስ ግዢ የደንብ ልብስ ስፌት እና የስፖርት ትጥቅ
- ሎት 2፡- የፅህፈት አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የትምህርት አላቂ ዕቃዎች ለመዋዕለ ህፃናት የሚያገለግሉ የትምህርት ዕቃዎች የመጀመሪያ ህክምና መርጃ ዕቃዎች፣ ለቤተ-ሙከራ የሚያስፈልጉ ኬሚካሎች እና ዕቃዎች ለስፖርት የሚያስፈልጉ ዕቃዎች
- ሎት 3፡- የፅዳት ዕቃዎች እና የህትመት ስራዎች
- ሎት 4፡- ጥገና (የኮምፒውተር የፕሪንተር ፎቶኮፒ እና ማባዢያ ማሽኖች) የውሃ ቧንቧ መስመር ጥገና፣ የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና የበርና መስኮት ጥገና ዴስኮች የቢሮ ፓርቲሽን ስራ የግቢ ቴራዞ ንጣፍ ስራ ከነአቅርቦቱ
- ሎት 5፡ የኤሌክትሮንክስ ግዢ (ኮምፒውተር፣ ላፕ ቶፕ ፕሪንተር እና ሴኪውሪቲ ካሜራ እና ከነገጠማው ላሚኔተር እስካነር
- ሎት 6፡- የሰራተኞች መስተንግዶ ግዢ እነዚህን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ስመሳተፍ የምትፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. በየዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. በአቅቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/ ማቅረብ የሚችሉ።
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች የተዘጋጀው ለጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበት ሎት1፡- 16,000 ሎት 2፡ 20,000 – 10,000 2,536-400 ሎት3፡ 24,000 – 3,600 ሎት4፡ 2000-20,000 ሎት5፡- 34,160 ሎት 6፡ 23,232.00 ብር ሲሆን በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ /CPO/ በቀለም አምባ ቅ/አ/አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ስም በማስያዝ ከጨረታው ሰነድ ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል ሲፒኦ/CPO/ ያላስያዘ ተወዳዳሪ ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።
5. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት አጓጉዞ የት/ቤቱ ንብረት ክፍል ውስጥ ያስረክባል።
6. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በት/ቤቱ የዕለት ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰነዱ ላይ በመሙላት ለዚህ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 4 ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዋጋ ሞልቶ እና የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም አድርጎ የማያቀርብ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም።
8. የጨረታ ሣጥን በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም በቢሮ ቁጥር 4 ውስጥ ይከፈታል።
9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን አላቂ ዕቃዎች ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ ከአንድ ቀን በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።
10. የጥቃቅንና አነስተኛ ልዩ አስተያየት የሚያገኙት ባመረተው ምርት እና በምርቱ ላይ እሴት በጨመሩት ብቻ ሲሆን ሌሎች እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ ገዝተው CPO አስይዘው ይወዳደራሉ።
11. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ት/ቤቱ የዕቃዎቹን ብዛት 20% የመጨመር /የመቀነስ/ መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. የጨረታው አሸናፊ መሆንዎ ሲታወቅ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 10% CPO በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
አድራሻ፡- ቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስትያን ፊት ስፌት ባስው መንገድ ገባ ብሎ ሼህ ሆጀሌ መስጊድ አጠገብ
ስልክ፡- 0112-30-41-55
የቀለም አምባ ቅድመ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-02
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-03 12:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Kelem Ameba Primary & Middle School
- Buyer address: ሩፋኤል ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት ባለው መንገድ ገባ ብሎ ሼህ ሆጀሌ መስጊድ አጠገብ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
- Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
- Posted at: 2026-08-22T08:16:26.000Z