Textile, Garment and Leather
የካራማራ የመ/ደ/ት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ለ2019 ዓ.ም. ለመማር ማስተማር የሚውሉ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ለመጀመሪያ ግዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የካራማራ የመ/ደ/ት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ለ2019 ዓ.ም ለመማር ማስተማር የሚውሉ የጽዳት ዕቃዎች፤ ለአስተዳደር ሰራተኞች የደንብ ልብስ፤ የእስቴንሸነሪ አቃዎች፤ አላቂ የትምርት ግብአቶች፤ ቋሚ የቢሮ አቃዎች /ፈርኒቸር/ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ
- ሎት1 የደንብ ልብስ
- ሎት2 አላቂ የቢሮ ግብአቶች
- ሎት3 የጽዳት እቃዎች
- ሎት4 የህክምና እቃዎች
- ሎት5 አላቂ የትምህርት ግብአቶች
- ሎት6 ለጥገና የሚውሉ ግብአቶች
- ሎት7 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት8 ቋሚ የቢሮ እቃዎች (ፈርኒቸር)
- ሎት9 ኮምፒዩተር ጥገና
- ሎት 10 ህትመት ስራዎች
በየዘርፉ የተሰማራችሁ ተጫራቾች
1/ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2/ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስተር ባዘጋጀው የእቃ እና የአገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
3/ ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ እና የvat ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው መረጃ የሚያቀርቡ።
4/ ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚጫረቱበት የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር /300/ ሶስት መቶ ብር ለእያንዳንዱ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት የመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ዘወትር የስራ ሰዓት ካራማራ የመ/ደ/ት/ቤት የፋ/ግ/ን/አሰ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
5/ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር በሎት የተቀመጠ ሲሆን፤ በእስቴሺነሪ አላቂ የጽፈት መሳሪያዎች /የምትወዳደሩ /5000/ አምስት ሺህ ብር በደንብ ልብስ የምትወዳደሩ /5000/ አምስት ሺህ ብር በጽዳት አቃዎች የምትወዳደሩ /5000/ አምስት ሺህ ብር ቋሚ እቃዎች ፈርኒቸር/የምትወዳደሩ /10,000/ አስር ሺህ ብር የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች /10,000/ አስር ሺህ ብር አላቂ የትምህርት ግብአቶች ላይ የምትወዳደሩ /5000/ አምስት ሺህ ብር የህክምና እቃዎች ላይ የምትወዳደሩ /3000/ሶስት ሺህ ለጥገና የሚውሉ ግባአቶች ላይ የምትወዳደሩ /4000/አራት ሺህ ብር ኮምፒውተር ጥገና ላይ የምትወዳደሩ /5000/ አምስት ሺህ ብር የህትመት ስራዎች ላይ የምትወዳደሩ /3000/ ሶስት ሺህ ብር /CPO/ በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
6/ ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት የሚጫረቱበት ዋጋ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ኦርጅናል እና ኮፒ በማድረግ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 3፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ በግልፅ ይከፈታል።
7/ ተጫራቾች ናሙና ሳምፕል/ማቅረብ ይኖርባቸዋል/ናሙና/ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይሆናል።
8/ የጨረታው አሸናፊ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ማስያዝ ይኖርባቸዋል
9/ መ/ቤቱ ለጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል ጀርባ ወረዳ 04 ጽ/ ቤት አለፍ ብሎ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0111 235 982 ወይም 0111 268 654
ካራማራ የመ/ደ/ት/ቤት የፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር
Tender details
- Deadline: 2026-09-03
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-03 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Karamara Elementary School
- Buyer address: አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በልደታ ክ/ከ/ወ/03 ካራማራ የመጀ/ደ/ት/ቤት ፣ ሌ/ኮ አብዲሳ አጋ ቅድመ አንደኛ ቀበሌ 37 ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት አብነት አደባባይ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
- Posted at: 2026-08-22T09:15:05.000Z