Food Items and Drinks
የሀላባ ዞን ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች ቀለብ አገልግሎት የሚውል የእህል አቅርቦቶች በየወሩ ለሚያቀርቡ አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ተጫራች ለመስጠት ይፈልጋል
Description
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የሀላባ ዞን ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም ለህግ ታራሚዎች ቀለብ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች በሠንጠረዡ ውስጥ የተመለከቱትን የእህል አቅርቦቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በቅድሚያ ለአንድ ዓመት በሚቆይ የአቅርቦት ጊዜ ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ በአቅራቢና ተቀባይ መካከል በሚደረገው የውል ስምምነት መሠረት እስከ ሶስት ዓመታት ለሚደርስ ጊዜያት ማለትም እስከ ሰኔ 2020 ድረስ እየተራዘመ የሚሰራ የግዥ ሂደት እንዳለ ታሳቢ በማድረግ፤ በማዕቀፍ ስምምነት በየወሩ ለሚያቀርቡ አቅራቢዎች በጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ተጫራች ለመስጠት ይፈልጋል።
ስለሆነም
|
ተ.ቁ
|
የአቅርቦቱ አይነት
|
መለኪያ
|
የአቅርቦት መጠን
|
የማቅረቢያ ጊዜ
|
ርክክቡ የሚፈፀምበት ቦታ |
ለአቅርቦቱ በማዕቀፍ ስምመነቱ መሠረት በቅድሚያ ለ01 ዓመት ቆይታ ጊዜ ከ... እስከ |
|
1 |
ነጭ ጤፍ (100 ኪ/ግ) |
ኩንታል |
ከ 15 - 20 ኩንታል |
ወር በገባ ከ25 - 30 |
ማረሚያ ተቋም |
ከ 15/12/18-30/10/2019 |
|
2 |
ነጭ ቦቆሎ (100 ኪ/ግ) |
ኩንታል |
ከ 43 - 60 ኩንታል |
ወር በገባ ከ25 - 30 |
ማረሚያ ተቋም |
ከ 15/12/18-30/10/2019 |
|
3 |
ስንዴ (100 ኪ/ግ) |
ኩንታል |
ከ 10 - 12 ኩንታል |
ወር በገባ ከ25 - 30 |
ማረሚያ ተቋም |
ከ 15/12/18-30/10/2019 |
|
4 |
ባቄላ (100 ኪ/ግ) |
ኩንታል |
ከ 5 - 8 ኩንታል |
ወር በገባ ከ25 - 30 |
ማረሚያ ተቋም |
ከ 15/12/18-30/10/2019 |
|
5 |
ዳጉሳ (100 ኪ/ግ) |
ኩንታል |
ከ 10 - 13 ኩንታል |
ወር በገባ ከ25 - 30 |
ማረሚያ ተቋም |
ከ 15/12/18-30/10/2019 |
መመዘኛዎችና የጨረታው መስፈርቶች፡-
1) በየመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው/ላት፤ የዘመኑን ግብር የከፈለች፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ያለው/ላት፤ ከማንኛውም ግብርና ታክስ ከፋይነት ነፃ እንዲሆኑ ከተፈቀደላቸው ድርጅቶችና ዩኒየኖችና ተመሳሳይ የንግድ ድርጅቶች ባስተቀር የ VAT 15% ተመዝጋቢ የሆነና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ሊያቀርቡ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤
2) ተጨራቾች ለሚጫራቱበት አቅርቦት በቀደምት የሥራ ዘመን ተጫርተው በማሸነፍ ለማረሚያ ተቋማት ወይም ለሌሎች መንግስታዊና ሕዝባዊ ድርጅቶች ለ01 (አንድ) አመት እና ከዚያም በላይ ለሆነ ጊዜያት ያለእንከን ስለማቅረባቸው የመልካም ሥራ አፈፃፀም ደብዳቤ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ከሌሎች መጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤
3) አሸናፊው ተጫራች ለአቅርቦቱ ከላይ በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሠረት በቅድሚያ ከነሀሴ 1/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለ11 (አስራ አንድ) ወራቶች በየወሩ ለማቅረብ ህጋዊ የውል ሰነድ የሚፈርምና በቅድሚያ ለመጀመሪያ ጊዜ የአሸናፊው ነጠላ ዋጋ እንደተጠበቀ ሆኖ በየጊዜው የእህልም ሆነ የሌሎች ዕቃዎች ዋጋ ሲቀንስ ለመንግስት በመቀነስ፣ ሲጨምር በማዕቀፍ ግዥዎች በተፈቀደው የዋጋ ማስተካከያ መመሪያ መሠረት ተጠቃሚ ሆኖ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሚሆን፤
4) ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የሀላባ ቁሊቶ ማረሚያ ተቋም ግዥና ፋይናንስ ንብ/አስ/ የሥራ ሂደት ቢሮ በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በነፃ መውሰድ የሚችሉ ሲሆን፤ የጨረታ ማስከበሪያን በሚመለከት ለሰብል ዓይነቶች ከጠቅላላ አቅርቦት ዋጋ 2% የብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ/ CPO/ተመሳሳይ ሰነድ በማሰራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5) ተጫራቾች ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አሥራ አምስት) ተከታታይ ቀናት የእያንዳንዱን እህል የአንዱን ኩንታል እንዲሁም ቃሪያ/ዛሌ በርበሬ በኪሎ ግራም ነጠላ ዋጋ ከነማስረጃው ኮፒዎች ጋር በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ አዘጋጅተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6) ተጫራቾች የእህል ዓይነቶችን ናሙና የማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው መዘንጋት የለባቸውም፤
7) ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11:30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4:30 ሰዓት በማረሚያ ተቋሙ ቅጥር ግቢ አዳራሽ/ቢሮ የሚከፈት መሆኑን ስንገልጽ ዕለቱ የበዓላት የዕረፍት ቀን ከሆነ በማግስቱ በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት መሆኑን እያሳሰብን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ልዩ ልዩ የአቅርቦት ሁኔታ፣ የጥራት ደረጃ እና ሌሎች መረጃዎችን በተመለከተ ተጫራቾች ስልክ በመደወል ወይም ሀላባ ቁሊቶ በሚገኘው የተቋሙ ፋይናንስ በመገኘት ቅድመ-መረጃ መውሰድ ይኖርባቸዋል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ 0927 101 112 (0916 679 661) ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን።
የሀላባ ማረሚያ ተቋም
Tender details
- Deadline: 2026-09-05
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 11:30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-07 12:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4:30
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Halaba Zone Kulito Correctional Facility
- Bid bond: 2% የብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ/
- Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
- Posted at: 2026-08-22T09:17:16.000Z