Textile, Garments and Uniforms

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ምስራቅ በር ቁ.1 የመጀ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የግዥ ጨረታ ማስታወቁያ
መለያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም.

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ምስራቅ በር ቁ.1 የመጀ/ደ/ት/ ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሎት ደንብ 1ልብስ ሎት 2. ደንብ ልብስ ስፌት ሎት 3. አላቂ የቢሮ እቃ ሎት 4. ህትመት ሎት 5. የህክምና እቃዎች ሎት 6. አላቂ የትምህርት እቃ ሎት7. የጽዳት እቃዎች ሎት 8. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ሎት 9. ለፕላንት ማሽነሪ ጥገና ሎት 10. ለስልጠና ግብዓት ሎት 11. ለፕላንት ማሽነሪ እቃ ሎት 12. ለተገጣጣሚ ቋሚ እቃ አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት ተመዝግበው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

3. የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ።

4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ።

የሎት ቁጥር

የሎት ዝርዝር

 

የተጠበቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብር

ሎት1

ደንብ ልብስ

 

8000 (ስምንት ሽህ ብር)

 

ሎት2

ደንብ ልብስ ስፌት

 

1000 (አንድ ሽህ ብር)

 

ሎት3

አላቂ የቢሮ እቃ

 

3000 (ሶስት ሽህ ብር)

 

ሎት4

ህትመት

 

2000 (ሁለት ሽህ ብር)

 

ሎት5

አላቂ የህክምና እቃ

 

3000 (ሶስት ሽህ ብር)

 

ሎት6

አላቂ የትምህርት እቃ

 

4000 (አራት ሽህ ብር)

 

ሎት7

አላቂ የጽዳት እቃዎች

 

6000 ( ስድስት ሽህ ብር)

 

ሎት8

ልዩልዩ መሳሪያዎች

 

3000 (ሶስት ሽህ ብር)

 

ሎት9

ማሽነሪ ጥገና

 

1000 (አንድ ሽህ ብር)

 

ሎት10

የስልጠና ግብአት

 

1000 (አንድ ሽህ ብር)

 

ሎት11

ለፕላንት ማሽነሪ እቃ

 

5000(አምስት ሽህ ብር)

 

ሎት12

ለተገጣጣሚ የቢሮ እቃች

 

5000 (አምስት ሽህ ብር)

 


6. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 5 ቀርበው መውሰድ ይችላሉ።

7. ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ 10 (በአስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነድ ዋናውን እና ኮፒውን ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

8. ጨረታ በ10ኛው ቀን በ10፡00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 10፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

9. ተጫራቾች ሲያሸንፉ የውል ማስከበርያ 10 ፐርሰንት ማስያዝ አለባቸው፡፡

10. ተጫራቾች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት ናሙና የሚቀርቡዋቸውን እቃች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። አማራጭ ናሙና ማቅረብ ከውድድር ውጭ ያደርጋል።

11.የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት በት/ቤቱ ንብረት ክፍል ግቢ ማድረስ አለበት።

12. የተለዩ እቃዎችን አንድ የዋጋ ዝርዝር ላይ የተለያዩ እቃዎች ዋጋ መሙላት አይቻልም፡፡

13. መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተረጋገጠ ነው።

14.መስሪያ ቤቱ 20 ፐርሰንት መጨመርም ሆነ መቀነስ መብቱ የተረጋገጠ ነው። አድራሻ ፤ ጉርድ ሾላ 500 ሜትር ወደ ውስጥ ገባ ብለው ጉሊት አካባቢ ስ.ቁ 011 667 7472

በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ምስራቅ በር ቁ.1 የመጀ/ደ/ት/ ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-02
  • Bid closing time: 16:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ በ10ኛው ቀን በ10፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-02 16:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ በ10ኛው ቀን በ10፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Mistak Ber No. 1 Junior School
  • Buyer address: ጉርድ ሾላ ከንግድ ባንክ 500 ሜትር ገባ ብሎ ገበያው አጠገብ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: በየሎቱ 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
  • Posted at: 2026-08-22T09:47:09.000Z
← Back to all tenders