Textile, Garment and Leather

በምሥራቅ ወለጋ ዞን የዋዩ ቱቃ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በወረዳው ሥር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በምሥራቅ ወለጋ ዞን የዋዩ ቱቃ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በወረዳው ሥር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል፡-

1. ለደንብ ልብሶች ከነማሰፊያው

2. ለጽሕፈት መሣሪያዎች

3. ለጽዳት መሣሪያዎች

4. ለኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች፤ ለመኪናና ሞተር ሳይክል ጎማዎች

5. ለቋሚ ዕቃዎች፤ ለመኪና እና ለሞተር ሣይክል ጥገና ከዚህ በታች ያለውን ምዘናዎችን የሚያሟላ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

1. የ2018 ዓ/ም የንግድ ግብር የከፈሉና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ የንግድ ዘርፍ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የቫት ስሌቱን አብሮ ሠርቶ ማቅረብ የሚችሉና ቫቱ ካልተጨመረበት ተቀባይነት የለሌው መሆኑን መረዳት የሚችሉ፡፡

4. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

5. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ /ቢድ ቦንድ/ በባንክ የተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) 10000 (አስር ሺህ) ማስያዝ የሚችሉ፡፡

6. ደረጃውንና ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ በጊዜ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

7. አስተማማኝና ጥራት ለሌላቸው ዕቃዎች ተጠያቂነትን የሚወስዱ፡፡

8. አንዱ ተጫራች በሚያቀርበው ዋጋ ላይ በ% ተንተርሶ ዋጋ መቀነስም ሆነ መጨመር የማይቻል መሆኑን፡፡

9. ተጫራች እስከ 21/1/2019 ዓ/ም ድረስ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ) ለዋዩ ቱቃ ወረዳ ገቢዎች ባለሥልጣን ጽ/ቤት በመክፈል የጨረታ ሰነድ በመንግሥት የሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡

10. ተወዳዳሪዎች የተጠየቁትን ማስረጃ በሙሉ እያንዳንዱን ሎት ቴክኒካልና ፋይናንሻል ኦርጂናሉንና ፎቶ ኮፒውን ለየብቻ በማድረግ ስሙን፣ ስልኩን፣ አድራሻውን ጽፎበትና የድርጅቱን ማሕተም አድርጎበት ሁሉን በአንድ ትልቅ በሰም በታሸገ ፖስታ ውስጥ በማድረግ በ22/1/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 22/1/2019 ዓ/ም ተወዳዳሪዎች፣ ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ወይም እነርሱ በሌሉበትም ከጠዋቱ በ4፡30 ላይ ውድድሩ ይካሄዳል፡፡

11. ተወዳዳሪዎች ጨረታውን ካሸነፉ ከታወቀ ባንክ (ኢንሹራንስ) 10% ፐርፎርማንስ ቦንድ በማቅረብ ያሸነፉትን ዕቃዎች በሙሉ እስከ ዋዩ ቱቃ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ ለማምጣት የሚገደዱ ይሆናል፡፡

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስለ ጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ቢያስፈልግ 09-17-88-91-38 / 0913 301 411

በምሥራቅ ወለጋ ዞን የዋዩ ቱቃ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-10-02 10:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: East Wellega Zone Wayu Tuka Woreda F/E/D/Bureau
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
  • Posted at: 2026-08-22T09:52:53.000Z
← Back to all tenders