Spare Parts and Car Decoration Materials
የሲዳማ/ክ/ስራና ክህሎት ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ የተለያዩ ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ
የሲዳማ /ክ/ስራና ክህሎት ቢሮ ለ2019 በጀት ዓመት በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች የኪችን ፈርኒቸር - የኪችን ዕቃዎች (የገበታ ዕቃ)፤ የመኪና ማስዋቢያ ዕቃዎች የጽህፈት መሳሪያዎች እና የጽዳት ዕቃዎች የመኪና ጥገና ጋራዥ (በሀዋሳ ብቻ ላሉ ጋራዦች) ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች ለመግዛት ስለሚፈጽም በዘርፉ ፍቃድ ያላቸውን ድርጅቶች አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምሰክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
2. የዘመኑን ግብር የከፈለና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው።
3. በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች ዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ ማንኛውም ተጫራች መሳተፍ ይችላል።
4. የተዘጋጀ ጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከመ/ቤቱ የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በመቅረብ ሠነዱን የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር ከፍለዉ መውሰድ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቬሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንሺያል የጨረታ ሰነድን ለብቻ በተለያ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለእያንዳንዱ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኢንቬሎፑ የውጭ ገጽ ዋና ኦርጂናል ወይም ኮፒ ብሎ በመፃፍና አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ሲሆን ሠነድ የሚያስገቡበት በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በፊት ብቻ ይሆናል፡፡ ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጧቱ በ3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የግዥና ንብረት ቡድን ሁለተኛ ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 01 በግልጽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም 16ኛ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፊተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለፅሕፈት መሳሪያና ለጽዳት ዕቃዎች 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ቤድ ወንድ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለመኪና ማስዋቢያ ዕቃዎች 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO፤ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረት ቢድ ቦንድ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የኪችን ዕቃዎች፤ 35,000 (ሰላሳ አምስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ቢድ ቦንድ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የመኪና ጥገና ጋራዥ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ቢድ ቦንድ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
11. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ቢድ ቦንድ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
12. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የኪችን ዕቃዎች (የገበታ ዕቃዎች) 40,000 (አሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ቢድ ቦንድ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
13. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የኪችን ዕቃዎች 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ ቢድ ቦንድ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
14. ጨረታውን በከፊል መጫረት የሚፈልግ ተጫራች ከተዘረዘሩት የዕቃ አይነቶች አንድ ወይም ከአንድ በላይ መርጦ መጫረት ይቻላል ለመኪና ጥገና ተጫራች ጋራዦች ግን መወዳደር የሚቻለው ሁሉንም የጥገና አይነት ስራ መሆን አለበት።
15 በጨረታው ለመሳተፍ ሚፈልግ ጉ/አቅራቢዎች/ ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በስልክ ቁጥር 046-212-21-74 ወይም 046-212-14-61 ዘወትር በስራ ሰዓት ማግኘት
16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
17. ጨረታ ያሸነፈው ድርጅት ዕቃዉን በራሱ ወጪ አጓጉዞ ወደ ተዘጋጀዉ ቦታ በማስገባት እስከ ተከላ መስራት አለባቸው።
የመ/ቤቱ አድራሻ፡- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፊት ለፊት ከሌዊ ሆቴል ዝቅ ብሎ ከሲዳማ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጎን ባለው ህንጻ ሁለተኛ ህንጻ 01 ቁጥር
የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስራና ክህሎት ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-09-07
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጧቱ በ3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-07 12:00
- Bid opening (note): ይህ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጧቱ በ4፡00 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: የሲዳማ/ብ/ክ/መ/ስራና ክህሎት ቢሮ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 22, 2026)
- Posted at: 2026-08-22T10:15:24.000Z