Building and Finishing Materials

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለአርማታ ዉህድ እና የብሎኬት ማምረቻ ማዕከል ስራ አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች ማለትም ጠጠር (00፣ 01 እና 02) እና የወንዝ አሸዋ ቀይ አሸዋ እና ኮሚቼ (ፑሚስ) ገላን ለሚገኘው የማምረቻ ማዕከል ድረስ ከሚያቀርብለት አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የማዕቀፍ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/ዕ.ግ/06/12/18

1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለአርማታ ዉህድ እና የብሎኬት ማምረቻ ማዕከል ስራ አገልግሎት የሚውሉ ግብዓቶች ማለትም ጠጠር (00፣ 01 እና 02) (ሎት 1) እና የወንዝ አሸዋ ቀይ አሸዋ እና ኮሚቼ (ፑሚስ) (ሎት 2) ገላን ለሚገኘው የማምረቻ ማዕከል ድረስ ከሚያቀርብለት አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/ዕ.ግ/06/12/18 በ2(ሁለት) ሎት ተጫራቾችን አወዳድሮ የማዕቀፍ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

2. ኮርፖሬሽኑ ለአርማታ ውህድ እና የብሎኬት ማምረቻ መዕከል ስራ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ መጠን ያላቸዉ ግብዓቶች ግዥ ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውንና የግብኣቶቹን ዋጋ በተለያዩ ፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።

3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የማዕቀፍ ግዢ ሥነ-ሥርዓትና ይህንነ አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈፃጸም መመሪያ መሠረት ሲሆን ተጫራቾች ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ በዘርፉ የስራ ልምድ ያላቸው እንዲሁም የግብር ከፋይ ማስረጃ እና ክሊራንስ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

4. የተሟላ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺ ብር/ በመክፈል  የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው የኮርፓሬሽኑ ዋና መ/ቤት ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።

5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 201 ለዚሁ አገልግሎት ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 30ኛው ቀን ወይም መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺ ብር) በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ በባንከ በተመሰከረለት የባንክ ዋስትና ወይም ሲፒኦ በፌደራል ቤቶች ኮፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው። ከጨረታው መክፈቻ ዕለትና ሰዓት ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተደደር ዳይሬክተር 2ኛ ፎቅ በሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

6. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ

ዌብሳይት /Website www.fhc.gov.et

የፖስታ ሣ.ቁ P.O. Box 299

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-09-23
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-23 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Federal Housing Corporation
  • Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 1,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T08:50:35.000Z
  • Buyer website: https://www.fhc.gov.et
← Back to all tenders