Textile, Garments and Uniforms

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ ደንብ ልብሶች፣ የደንብ ልብስ ስፌት፣ አላቂ የፅህፈት ዕቃዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ቋሚ ዕቃ፣ የህትመት ውጤቶች፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ልዩ ልዩ ዕቃዎችና የጥገና መለዋወጫ ዕቃ፣ የፓርቲሽን ጥገና ስራ፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ መድሀኒትና ሪኤጀንት፣ የህክምና መሳሪያዎች እና የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃዎችን መ

Description

1ኛ ዙር የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ የ2019 በጀት አመት 1ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት1.ደንብ ልብሶች 1.1 የደንብ ልብስ ስፌት
  • ሎት2.አላቂ የፅህፈት ዕቃዎች
  • ሎት3.የጽዳት እቃዎች
  • ሎት 4.ቋሚ ዕቃ
  • ሎት 5.የህመት ውጤቶች
  • ሎት 6.ኤሌክትሮኒክስ
  • ሎት 7.ልዩ ልዩ ዕቃዎችና የጥገና መለዋወጫ ዕቃ
  • ሎት 8.የፓርቲሽን ጥገና ስራ
  • ሎት 9. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና
  • ሎት 10.መድሀኒትና ሪኤጀንት
  • ሎት11. የህክምና መሳሪያዎች
  • ሎት 12. የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ማስወገድ አገልግሎት

በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።

  1.  ከላይ ከተራ ቁጥር 1-12 ለተጠቀሰው ዕቃ በዘርፉ ሕጋዊና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  3. ቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
  4. ቲን ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
  5. ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆኑን በአቅራቢዎች ዝርዝር www.ppa.go.et online ላይ የተመዘገበ መሆኑን ጨረታው ሲከፈት ወዲያውኑ የሚረጋገጥ ይሆናል። online ላይ ሲታይ ካልተገኝ ከወድድር ውጪ/ውድቅ ይደረጋል።
  6. ተጫራቾች የገዙትን መደበኛ የጨረታ ሰነድ በተጫራች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች በአግባቡ ተሞልቶና በድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ተደርጎበት ከዋጋ መሙያው ጋር ሙሉ መደበኛ የጨረታ ሰነዱ/መመሪያው መመለስ አለበት። የጨረታ ሰነዱን/መመሪያውን ያልመለሰ ከውድድር ውጪ ይሆናል።
  7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከፓስተር አደባባይ 50 ሜትር ገባ ብሎ ባለው ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 በመገኘት ብር 250 /ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይቻላል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎቶች ከ0.5 እስከ 2 % ሲሆን ሎት 19.500 ፤ ሎት2.7,000 ፤ ሎት 3.9,000 ፤ ሎት4.11,000 ፤ሎት5.5,000 6.12,000 ሎት7 9,000 ፤ ሎት8.8,500 ሎት 9.4,000 ሎት 10. 17,000 ፤ ሎት 11.14,000 ሎት 12 1,000 ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ CPO ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያ ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሰነዱን ማቅረብ አለባቸው። በ11ኛው ቀን የጨረታ ማስገባት አይቻልም።
  9. ተጫራቾች እያንዳንዱን የሚሸጡበትን ነጠላ ዋጋና የጠቅላላውን ዋጋ ከነቫቱ በመግለጽ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በየሎቱ ለየብቻ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውንና የጨረታውን የሎት አይነት ፖስታው በመጥቀስ ከፓስተር አደባበይ 50 ሜትር ገባ ብሎ ባለው ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 403 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  10. ተጫራቾች በዘርፋቸው የተጠቀሰውን ዕቃ በሙሉ መጫረት ይችላሉ ።
  11. ሁሉም ተጫራቾች ሰነዱን ሞልተው ሲያስገቡ ናሙና የሚጠይቁ ዕቃዎችን የዕቃውን ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው። ናሙና ካላቀረቡ ተቀባይነት የለውም።
  12. የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ የመጨረሻው ቀን በ10 ኛው ቀን እስከ ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሸጎ በእለቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4ተኛ ፎቅ በጤና ጣቢያው አዳራሽ ውስጥ ይሆናል። በ11ኛው ቀን የጨረታ ሰነድ ማስገባት እይቻለም።
  13.  ቀጣዩ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተራ ቁጥር 12 በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ተፈፃሚ ይደረጋል።
  14.  ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
  15.  በጥቃቅን የተደራጁ አካላት የሚያቀርቡት የዋስትና ደብዳቤ የተደራጁበት ዘርፍ በግልፅ የተቀመጠና አምራች ከሆነ የሚያመርተው ዘርፍ አምራች መሆኑን በግልፅ የተቀመጠና ደብዳቤውን ለመፈረም ስልጣን በተሠጠው አካል የተፈረመና ስልክ ቁጥር ያለው እና የተደራጀው የሚሰራበት ቦታ ተጠቅሶ የዋስትና ደብዳቤው ለጨረታ ማስከበሪያና ለውል አለባቸው።
  16.  አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም።
  17.  የጨረታ አሸናፊነቱ ሲረጋገጥ በግዥ ደንብና መመሪያ መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውል ለመዋዋል ፈቃደኛ የሆነ እና እቃውንም ለማቅረብ በግዥ ደንብና መመሪያ መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ።
  18. ጨረታ ተወዳድሮ አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ውል ለመዋዋል ሲመጡ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% cpo የውል ማስከበሪያ አሰርተው መምጣትና መዋዋል አለባቸው።
  19. አሸናፊ ተጫራች ውል ከወሰደ በኋላ እቃውን በተቋሙ ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንፖርት የማቅረብና ለንብረት ከፍሉ ማስረከብ ግዴታ አለበት። 
  20. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው። መድሀኒት ላይ ተቋሙ ያስቀመጠውን ዩኒት/አስፔስፊኬሽን መሰረዝ መቀየር ከውድድር ውጪ ያደርጋል።

ማሳሰቢያ፡- ቋሚ እቃዎችና የህክምና መሳሪያዎች ተጫራቾች ተቋሙ ባስቀመጠው እስፔስፊኬሽን መሰረት አስቀድሞ ከሰነዱ ጋር የእቃውን ፎቶና ካታሎግ ማስገባትና የእቃው ሙሉ መረጃ የተሰራበት የእቃ አይነት ተገልፆ ማስገባት አለባቸው። የጤና ጣቢያው ጥራት ኮሚቴ የዕቃውን ጥራት ደረጃ ለማየት ሲመጡ ወርክ ሾፕ የማሳየት ግዴታ አለበት። የሁሉንም ሎቶች ስፔስፊኬሽን ( ፍላጎት መግለጫ ) በጨረታ ሰነዱ በክፍል ስድስት (6) ማየት ይቻላል።

ስልክ ቁጥር፦ 0118-95-94-78/0930-69-56-68

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የወረዳ 6  ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-03
  • Bid closing time: 09:00
  • Bid closing (note): የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ የመጨረሻው ቀን በ10ኛው ቀን እስከ ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-03 09:30
  • Bid opening (note): የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ የመጨረሻው ቀን በ10ኛው ቀን እስከ ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Felege Meles Health Post
  • Buyer address: አ/ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ፈለገ መለስ ጤና ጣቢያ ከፓስተር ወረድ ብሎ ወደ ወረዳ 06
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 250.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T09:49:07.000Z
← Back to all tenders