Catering and Cafeteria Services
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የምዕራፍ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የሻይ ቤት መዝናኛ ክበብ፣ የጉልበት ሰራተኛ አገልግሎት እና የመኪና ጭነት ኪራይ አገልግሎት በ1ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001 /2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የምዕራፍ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ከመደበኛ በጀት በመንግስት ግዥ መመርያ መሰረት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሻይ ቤት መዝናኛ ክበብ፣ የጉልበት ሰራተኛ አገልግሎት እና የመኪና ጭነት ኪራይ አገልግሎት በ1ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የምዕራፍ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ግዢ ቢሮ ቁጥር 12 መውሰድ ትችላላችሁ።
|
ተ.ቁ |
የአገልግሎት አይነት |
ሎት |
የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና |
|
1 |
የሻይ ቤት መዝናኛ ክበብ |
1 |
1584 |
|
2 |
የተለያዩ የጉልበት ሰራተኛ አገልግሎት |
2 |
800 |
|
3 |
የመኪና ጭነት ኪራይ አገልግሎት |
3 |
800 |
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑ ግብር የከፈለ።
2. በዘርፉ የተሰማሩበት ንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው።
3 .አቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
4. የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
3. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ቫትን ጨምሮ በዝዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅራቢያ ቦታ በግልፅ ማስፈር እና መጨረሻ ቦታ ላይ ፊርማ እና ማህተም በመምታት በ 1ኦርጅናል እና 1 ኮፒ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሲሆኑ 10 ፐርሰንት የውል ማስከበርያ በማስያዝ እና የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል።
7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታ የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በወጣበት 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 15 ይከፈታል።
9. የውል ማስከበርያም ሆነ የጨረታ ማስከበርያ ብር በጥሬ ግንዘብ የምንቀበል መሆኑን እየገለፅን በባንክ የተረጋጋጠ ሲፒኦ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
10. ትምህርት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. በጉልበት ሰራተኞች ሎት ላይ የምትወዳደሩ በጥቅላላ አገልግሎት የሙያ ዘርፍ የተደራጁ እና ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል ወይም በተናጠል ለምትወዳደሩ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው እና የታደሠ መታወቂያ ያለው መሆን አለበት።
12. በመኪና ጭነት ኪራይ አገልግሎት ሎት ላይ ምትወዳደሩ የታደሠ ንግድ ፍቃድ እና የአሽከርካሪ የሙያ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል እና ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው መሆን የጠበቅበታል። ከዚህ በተጨማሪ በሽርክርና ማህበር ተደራጅቶ የሚሠራ እና ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል መወዳደር ይችላል።
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አንበሳ ጋራዥ በስተጀርባ ወይም ከዊንጌት ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ በስተቀኝ ከፖሊስ ካምፕ ከፍ ብሎ የምዕራፍ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ወይም ከአዲሱ ገበያ ዊንጌት በሚወስደው መንገድ በስተግራ በኩል ዜብራ መንገድ ተሻግሮ ከአገሪ ቱሉ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ዝቅ ብሎ ባለው ቀጭን መንገድ ገባ ብሎ ወደቀኝ ታጥፎ የምዕራፍ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 12።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-259 5671
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ ቢሮ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የምዕራፍ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-01
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛው ቀን 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-02 10:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Meraf General Secondary School
- Buyer address: ጉለሌ ክ/ከ/ወ/10 ሸጎሌ ከአንበሳ ጋራዥ በስተጀርባ ወይም ከዊንጌት ወደ አዲሱ ገበያ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
- Posted at: 2026-08-24T09:54:45.000Z