Water Pipes and Fittings

ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ ከBMZ ባገኘው ድጋፍ SI AGER- Sustainable Food Security & Resilience Building የተሰኘ ፕሮጄክት በቦረና ዞን፣ ድሬ ወረዳ ለሚገኙ ማህበረሰቦች የውሃ አቅርቦት ለማሻሻል የሚያስፈልጉ የሶላር ውሃ ፓምፕ ሲስተም ሙሉ ግዥና ተከላ (Complete Supply and lnstallation) እንዲሁም HDPE Pipes and Fitting

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ ከBMZ ባገኘው ድጋፍ SI AGER- Sustainable Food Security & Resilience Building የተሰኘ ፕሮጄክት በቦረና ዞን፣ ድሬ ወረዳ ለሚገኙ ማህበረሰቦች የውሃ አቅርቦት ለማሻሻል የሚያስፈልጉ የሶላር ውሃ ፓምፕ ሲስተም ሙሉ ግዥና ተከላ (Complete Supply and installation) እንዲሁም HDPE Pipes and Fittings በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የጨረታው የግዥ ዝርዝር

1. Solar Pump System Complete Supply and Installation

2. HDPE Pipes and Fittings

በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተገለጸው ዝርዝር መግለጫ (Specification)፣ መጠንና ብዛት መሠረት መቅረብ አለባቸው።

ስለሆነም የታደሰና ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን 300.00 ብር በመክፈል ከድርጅቱ መግዛት ይችላሉ።

ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 3% የሚሆን የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ ስም በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/የባንክ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው። የBid Bond ከጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ ተካትቶ መቅረብ ይኖርበታል።

የጨረታ ሰነዱን መግዛትና የጨረታ ሰነዱን ማቅረብ የሚቻለው የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ሲሆን፣ በአዲስ አበባ፣ መስቀል ፍላወር አደባባይ አካባቢ፣ ከቪላ ቨርዴ ሆቴል አጠገብ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ማቅረብ ይችላሉ።

የጨረታ ሰነዱ የሚቀርበው ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በአስረኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ የሚዘጋ ሲሆን፣ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡20 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱን የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፦

ስልክ: 011 558 3967 / 011 558 2328/ 09 13 39 98 17

ሁንዴ ኦሮሞ ግራስሩትስ ዴቨሎፕመንት ኢኒሼቲቭ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-01
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በአስረኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-01 10:20
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በአስረኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡20 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Hundee-Oromo Grassroots Development Initiative
  • Buyer address: አዲስ አበባ፣ መስቀል ፍላወር አካባቢ፣ ያሬድ ቤተክርስቲያን ጀርባ፣ በቪላ ቨርዴ ሆቴል ገባ ብሎ
  • Bid bond: 3%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Reporter (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T13:44:50.000Z
← Back to all tenders