Cleaning and Janitorial Equipment and Service
የወልዲያ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ2019 በጀት ዓመት የጽዳት እቃ፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ የመኪና እቃዎች እና ዘይትና ቅባት፣ የውሀ መለዋወጫ እቃ፣ የሠራተኞች ደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ፣ የተዘጋጁ ልብሶች እና ጫማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ወመትኮግዥገ-1/ 298 /2019
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የወልዲያ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለ2019ዓ.ም በጀት አመት፣ የጽዳት እቃ፣ የጽህፈት መሳሪያና የመኪና እቃዎች እና ዘይትና ቅባት የውሀ መለዋወጫ እቃዎችን የሠራተኞች ደንብ ልብስ ብትን ጨርቅ የተዘጋጁ ልብሶች ጫማ፤ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣው በጨረታ በማወዳደር ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ በየስራ ዘርፋቸው ፈቃድ ያላቸው መሆን አለበት፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
3. አሸናፊ ከሆኑ ወልዲያ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ድረስ በራሳቸው ወጪ ማስጫኛና ማውረጃ ችለው አጓጉዘው ማቅረብ የሚችሉ፣
4. ተጫራቾች አሸነፊነታቸው ከተገለፀላቸው ከ 5 የስራ ቀናት በኋላ ባሉት ተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ ቀርበው ውለታ መውሰድ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ አጠቃለው ካላስገቡ ምንም አይነት ክፍያ አይከፈልም።
6. ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ለጽህፈት መሳሪያ 7500 ለጽዳት እቃ 2700 ለብትን ጨርቅ 600 ለተዘጋጁ ልብሶች 1800 ለጫማ 2700፤ ለመኪና ዘይትና ቅባት 2000፡ ለመኪና እቃ 1000 በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ እና ከጨረታ ፖስታ ውስጥ አብሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. በጨረታ ሰነዱ የተቀመጠውን የስራ ዝርዝር በጥንቃቄ መሙላትና ጠቅላላ ድምር በማስቀመጥ የሚሞሉትን ዋጋ የቫት ያካተተ መሆን ይኖርበታል። ውድድሩም በየስራ ዘርፉ በሎት ነው።
8. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአየር ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ10 ቀን 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ገዝተው በመውሰድ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው የሚታሸገው ይህ ማስታወቂያ በአየር ከዋለበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀን መጨረሻ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ስአት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ ባይገኙ በመመሪያው መሰረት በሌሉበት ጨረታው ይከፈታል። ተጫራቾች የሞሉትንና ያሸነፉበትን እቃ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
10. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ ሆኖ በቀረበ ማንኛውም ፎርም ዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ /እስፔስፍኬሽን እንዲሁም የጨረታ ሰነዱ በታሸገበት ፖስታ ላይ ኦርጅናሉንም ሆነ ኮፒው ስማቸውን ፊርማቸውን የድርጅታቸውን ማህተምና ሙሉ አድራሻቸውን ሊነበብ በሚችል መልኩ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
11. የጨረታ መዝጊያ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ላቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሌላ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም።
12. እቃዎቹ በሙሉ ውድድሩ በሎት ነው።
13. ጨረታው የሚከፈትበት የመጨረሻው ቀን በዓልና ቅዳሜና እሁድ ቀን ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን እንደሚዞር ማወቅ፣ ጨረታው ከወጣ በኋላ የመክፈቻና የመዝጊያ ቀኑን ከመመሪያው ቀኑን የምናሳውቅ ሲሆን፤ ግልጽ ያልሆነ ካለ በአድራሻችን በአካልም ይሁን በስልክ መጠየቅ ይቻላል።
14. ተጫራቾች በራሳቸው ምክንያት ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ባይገኙ ያቀረቡት የጨረታ ሰነድ በመመሪያው መሰረት ባይገኙም በሌሉበት ይከፈታል።
15. የቫት ተመዝጋቢዎች የሆኑ እስከ ቫቱ ዋጋውን ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ያልሞላ ተጫራች ቢኖር ከውድድሩ ይሰረዛል።
16. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 033-331-2735
ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የወልዲያ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-11-23
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአየር ከዋለበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀን መጨረሻ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ስአት
- Bid opening: 2026-11-23 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአየር ከዋለበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ቀን መጨረሻ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ስአት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Woldia Teachers' Education College
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 (ሦስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Nov 07, 2026)
- Posted at: 2026-11-07T07:40:52.000Z
- Source: Qelal Tenders