Home Appliance and Supplies

ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል ከውጪ ያስመጣቸውን አገልግሎት የሠጡ ለረዥም ጊዜ የቆዩ ዕቃዎች ባለበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር አድራሻ፡-አዲስ አበባ ክ/ከተማ፡- ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09

ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል ከውጪ ያስመጣቸውን አገልግሎት የሠጡ ለረዥም ጊዜ የቆዩ ዕቃዎች ባለበት ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተጫራቾች በሆስፒታሉ በመገኘት እቃዎቹን በማየት የጨረታ ሠነዱን ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ትችላላችሁ።

ተጫራቾች፡-

1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ ቀናት ንብረቶች በሚገኙበት አድራሻ ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ድረስ በመገኘት በመመልከት የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ፖስታ ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር 25 ማስገባት ይኖርባቸዋል።

2. ጨረታው ማስታወቂያ በወጣ ከ10 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ ይከፈታል።

3. ሆስፒታሉ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ለተጫራቶች ምንም ኃላፊነት ሳይኖርበት ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

4. የዕቃዉ አይነት

  • የጣልያን የልብስ መተኮሻ
  • የጣልያን ጄኔሬተር
  • የጣልያን ፍሪጅ

ተጨማሪ ማብራሪያ ሲያስፈልግዎ 09 11 40 60 42 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
ተዘንአ አጠቃላይ ሆስፒታል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-09-02
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-02 14:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: TZNA General Hospital PLC
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Reporter (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T13:48:16.000Z
← Back to all tenders