Textile, Garments and Uniforms
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጉለሌ ፋና የመጀ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018 ዓ.ም
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጉለሌ ፋና የመጀ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋሉ፡፡
- 1ኛ. (ሎት 1) የደንብ ልብስና የስፖርት ትጥቆች
- 2ኛ. (ሎት 2) አላቂ የቢሮና የጽህፈት መሳሪያዎች የተለያዩ የፕሪንተር እና የፎቶኮፒ ቀለሞች ተዛማጅ ዕቃዎች
- 3ኛ. (ሎት 3) ህትመት
- 4ኛ. (ሎት 4) አላቂ የህክምና መርጃ እቃዎች
- 5ኛ. (ሎት 5) አላቂ የትምህርት እቃዎች
- 6ኛ. (ሎት6) አላቂ የጽዳት እቃዎች
- 7ኛ. (ሎት 7) የተለያዩመሳሪያዎች(የጥገና እቃዎች)
- 8ኛ. (ሎት 12) ቋሚ እቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግስሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ(Tin) ቁጥር ያላቸው፡፡
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
4.የአቅራቢዎች ዝርዝር በህጋዊነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ናሙና/ሳምፕል/ ለሚጠይቁ ዕቃዎች ማቅረብ የሚችል፡፡
6. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10% ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ላይ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝና ተዋውለው ዕቃዎችን በትምህርት ቤቱ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙበት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቫትን ጨምሮ በመግለፅ ዋናውን እና ኮፒውን በመሙላት በሶስት ወይም በአራት በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 09 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ናሙናዎች ጨረታው ከመከፈቱ ከሁለት ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
9. በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ አካላት ከሆኑ ሰነድ ለመውሰድ በሚመጡበት ጊዜ ከሚመለከተው አካል ወቅታዊ የሆነ፣ በጽ/ቤቱ ስም የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
10. ለጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በሚያመርቱት ምርት ብቻ ከሆነ ልዩ አስተያየት ይደረጋል፡፡
11. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ጉለሌ ፋና የመጀ/ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥ 04 በመገኘት የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
12. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ
- (ሎት 1)፡- 15,200 (አስራ አምስት ሺህ ሁስት መቶ ብር)
- (ሎት 2)፡-5,900.00 (አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር)
- (ሎት 3)፡- 1,800.00(አንድ ሺህ ስምንት መቶ ብር)
- (ሎት 4)፡-300.00 (ሶስት መቶ ብር)
- (ሎት 5)፡- 1,100.00(አንድ ሺህ አንድ መቶ ብር)
- (ሎት 6)፡- 13,000,00 (አስራ ሶስት ሺህ ብር)
- (ሎት 7)፡-2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)
- (ሎት 8)፡-4,000.00 (አራት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገተጠ /ሲፕኦ/ በታሸገ ኤንቨሎፕ አምጥተው ቢሮ ቁጥር 09 ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
13. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ ጠዋት 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
14. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
15. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ፡- ጉለሌ ፋና የመጀ/ደ/ት/ቤት ካኦ ጄጄ ዱቄት ፋብሪካ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር 0112 730842 / 0112 730825/0112730824
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጉለሌ ፋና የመጀ/ደ/ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-04
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-04 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Gulele Fana Elementary School
- Buyer address: ካኦ ጄጄ ዱቄት ፋብሪካ ፊት ለፊት
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T06:51:43.000Z