Textile, Garments and Uniforms

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የአፄ ልብነ ድንግል ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያገለግሉ ግብዓቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019ዓ.ም

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የአፄ ልብነ ድንግል ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ምበጀት ዓመት የሚያገለግሉ ግብዓቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊና ፍላጎት ያላችሁ አቅራቢዎች በየሎቱ ለተከፋፈሉ ዕቃዎች ከተራ ቁጥር ከ1-12 መስፈርቱን የምታሟሉ ተጫራቾች ተጋብዛችኋል።

  • ሎት 1የመምህራን አስተዳደር ሰራተኞች የደንብ ልብስና የደንብ ልብስ ስፌት
  • ሎት.2 አላቂ የቢሮ እቃዎች፡፡
  • ሎት.3.የህትመት ስራዎች።
  • ሎት 4አላቂ የህክምና እቃዎች።
  • ሎት 5 አላቂ የትምህርት እቃዎች።
  • ሎት 6.አላቂ የጽዳት እቃዎች
  • ሎት.7.የጥገና እቃዎች
  • ሎት.8.የተለያዩ ማጣቀሻ መፅሐፍቶች::
  • ሎት.9.ቋሚ እቃዎች
  • ሎት.10. የት/ቤቱ አጥር ስራ በእንጨትና በቆርቆሮ ሚስማር
  • ሎት 11የመምህራን ማረፊያ አሮጌ ሶፋ ሙሉ እድሳት
  • ሎት.12.የሰራተኞች ክበብ ወይም ካፌ

ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የገበረ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው እንዲሁም ከሚያቀርቡት ዕቃ ወይም አገልግሎት ጋር የተዛመደ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

ማንኛውም ተጫራች የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ወይም በኤጀንሲው ድህረ ገፅ ላይ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።የጨረታ ማስከበሪያ በተመለከተ

  • ሎት 1 .28,000 / ሃያ ስምንት ሺህ ብር
  • ሎት 2 26,000 / ሃያ ስድስት ሺህ ብር/
  • ሎት 3 3,000 /ሶስት ሺህ ብር /
  • ሎት 4. 2,000 /ሁለት ሺህ ብር !
  • ሎት 5. 8,000 /ስምንት ሺህ ብር /
  • ሎት 6. 28,396.28 / ሃያ ስምንት ሺህ ሶስት መቶ መቶ ዘጠና ስድስት ብር ከሃያ ስምንት ሳንቲም
  • ሎት.7.12,000 /አስራ ሁለት ሺህ ብር/
  • ሎት.8. 6,000 / ስድስት ሺህ ብር/
  • ሎት.9. 20,000 / ሃያ ሺህ ብር/
  • ሎት.10. 2,000 / ሁለት ሺህ ብር
  • ሎት.11.2,000/ ሁለት ሺህ ብር/
  • ሎት.12. 26,452.80/ሃያ ስድስት ሺህ አራት ሃምሳ ሁለት ብር ከሰማኒያ  ሳንቲም/ 

2. በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼክ CPO እና የባንክ ዋስትና /bank guarantee/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸው ብር 50,000/ሃምሳ ሺህ ብር/ በላይ ለሆኑ ዕቃዎች የሚወዳደሩ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ለሚዘጋጀው የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200/ሁለት መቶ ብር በመክፈል ሰነዱን ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀናት በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ ማህተም ባረፈበት በታሸገ ኢንቨሎፕ በተዘጋጀው በጨረታ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1 ድረስ በመምጣት ማስገባት ይኖርባቸዋል።ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10%ውል ማስከበሪያ በማስያዝ ውል መዋዋል አለባቸው። በተጨማሪም ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በ15 ቀናት ውስጥ በአፄ ልብነ ድንግል ቅ አንደኛ፣አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ንብረት ክፍል አጠናቀው ማስገባት ይኖርባቸዋል። 

6. ተጫራቾች ዋጋ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም። ቢፈጠር ከፊት ለፊቱ ፊርማ ሊኖረው ይገባል።አለበለዚያ የተሞላው ዋጋ ቀባይነት አይኖረውም።

7. የጨረታ ሰነዱ አንዱ የጨረታ መመሪያ መሆኑን ተጫራቾች ሊረዱት የሚገባ ሲሆን በጨረታ ሰነዱ ላይ ያልተካተቱ ችግሮች ቢገጥሙ በግዥ መመሪያ የሚዳኝ ይሆናል።

8. ጨረታው የሚዘጋው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ታሽጎ የሚከፈትበት ቀን በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል።

9. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀናት ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀናት ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን የጨረታው መክፈቻ እና መዝጊያ ቀናት ይሆናል።

10. መስሪያ ቤቱ በግዥ ዝርዝር ከቀረበው የእቃ ብዛት ላይ 20% መቀነስና መጨመር መብትአለው።

11. አሸናፊ ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ትምህርት ቤቱ ድረስ ያቀርባል።

12. መስሪያቤቱ የተሻለ የአሰራር ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. የጥቃቅንና አነስተኛ ላይ የተደራጁ ተጫራቾች ልዩ አስተያየት የሚደረገው በሚያመርቱት ምርት ብቻ ሆኖ ከተደራጁበት ተቋም በሚያቀርቡት ደብዳቤ ይሆናል።

አድራሻ፡- ቀጨኔ መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን ዝቅ ብሎ ከባህታዊ ገ/መስቀል ቤት ፊት ለፊት ወይም ከወረዳ 4 አስተዳደር ከፍ ብሎ የሚገኝ አፄ ልብነ ድንግል ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ነዉ ።

ለበለጠ መረጃ ስልክቁጥር፡-011 155 2066 / 011 126 7552

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ትምህርት ጽ/ቤት የአፄ ልብነ ድንግል ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ /ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-03
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-04 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Atse Lebne Dingel Kindergarten & Primary School
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T07:02:48.000Z
← Back to all tenders