Spare Parts and Car Decoration Materials
ፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ኦሪጂናል የመኪና መለዋወጫ እቃዎች እና ሌሎች አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ
ማስታወቂያ ቁጥር 002/2019 ዓ.ም
ፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ኦሪጂናል የመኪና መለዋወጫ እቃዎች እና ሌሎች አገልግሎት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 ለሀገር አቋራጭ ኦርጅናል አውቶቢስ መለዋወጫ፤
- ሎት 2 የከተማ አውቶቢስ ኦርጅናል መለዋወጫ
- ሎት 3 ለውጭ ጥገና የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ኦርጅናል መለዋወጫ፤
- ሎት 4 ለልዩ የሀገር አቋራጭ አውቶቢሶች ጎማ 315/80/R/22.5 20PR እና የከተማ አውቶቢሶች ጎማ 295/80/R/22.5 18 PR መገዛት ይፈልጋል፤
- ሎት 5 የሰራተኛ ክበብ ኪራይ አገልግሎት፤
- ሎት 6 ዴስክቶፕ ኮምፒውተር እና ፕሪንተር
1. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር የስራ ቀናት ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ለእያንዳንዱ ሎት 1000 በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 በአካል በመምጣት መግዛት ይችላሉ።
2. ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ተጫራቾች በዘርፉ ንግድ ምዝገባና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ የብቃት ማረጋገጫ እና የአቅራቢዎች የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የንግድ መለያ ቁጥር (Tin ) ያላቸው፤ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ከሎት 1 እስከ ሎት 6 ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የሚያቀርቡትን የጨረታ ሠነድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ ዋና እና ኮፒ በሁለት ፖስታ በማዘጋጀትና በኤንቨሎፕ በማሸግ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ኃላፊነት በተሰጠው አካል ተፈርሞበት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
4. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ 2% ሲፒኦ /Bid Bond/ ወይም በባንክ የተመሰከረለት በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች ለሎት 4 ለእያንዳንዱ ሳምፕል ማቅረብ አለበት።
6. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡ዐዐ ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻው ቀን የዕረፍት ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይከፈታል።
7. አገልግሎታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከሜክሲኮ ወደ ልደታ ቤተክርስቲያን
በሚወስደው መንገድ ላይ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ስፊት ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡-ስልክ ቁጥር *-011-550 4564
ፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት
Tender details
- Deadline: 2026-09-07
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-07 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Public Service Employees' Transport Service Enterprise
- Buyer address: ከሜክሲኮ ወደ ልደታ ቤተክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ላይ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ነው
- Bid bond: ለእያንዳንዱ ሎት 2%
- Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎት 1000.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T08:43:21.000Z