Finishig Works
በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት የብላቴ ዙሪያ ወረዳ በሌላ ማዘጋጃ ቤት በኩል ኮብልስቶን ለማንጠፍ እና ድች ለማሰራት የሚችሉትን ህጋዊ ኮንትራክተሮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት የብላቴ ዙሪያ ወረዳ በሌላ ማዘጋጃ ቤት በኩል ኮብልስቶን ለማንጠፍ እና ድች ለማሰራት የሚችሉትን ህጋዊ ኮንትራክተሮችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ በዚህ መስክ የተሰማራችሁት ማሟላት የሚገባችሁ መስፈርቶች፤
1. በ2018 ዓ/ም ንግድ ፈቃዳቸው ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ አግባብነት ያለው የታደሰ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
2. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
3. CPO በባንከ የተረጋገጠ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
4. ጨረታ አሸናፊው የሚሆን ከጠቅላላ ዋጋ የቅድመ ክፍያ መጠን 30% በባንክ የተረጋገጠ የባንክ ጋራንት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
5. ጨረታው አሸናፍ የሚሆን ከጠቅላላ ዋጋ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
6. የሚሰራው ኮብልስቶን ማንጠፍ እና ድች ጥራቱን የተጠበቀ እና መ/ቤቱ የሚፈልገውን መስራት ይኖርበታል።
7. ለሚሰራው ኮብልስቶን ማንጠፍ እና ድች የጥራት ጉድለት ቢገኝ በራሱ ኪሳራ ለውጦ ጥራት ያለው ኮብልስቶን ማንጠፍ እና ድች የሚሰራ ይሆናል፡፡
8. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት የብላቴ ዙሪያ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር - 4 ቀረበው ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ። በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 8፡00 ሰዓት በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት የብላቴ ዙሪያ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ : ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ በሰም አሽገው ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሀጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 8፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ላይ ይከፈታል፤ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉልም፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0916165270/0961612750
በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት የብላቴ ዙሪያ ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-10
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-10 14:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ16ኛው ቀን 8፡30 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Bilate Zuria Woreda FEDB
- Bid bond: 200,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T08:43:23.000Z