Textile, Garments and Uniforms

የመስከረም ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 1/2019 ዓ.ም

የመስከረም ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ሎት 1. የደንብ ልብሶች ሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ሎት 3. የተለያዩ ህትመቶች ሎት 4, አላቂ የህክምና እቃዎች ሎት 5. አላቂ የትምህርት እቃዎች ሎት 6. ሌሎች አላቂ ዕቃዎች ሎት 7. ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ሎት 8. የሰራተኞች የመዝናኛ ክበብ (የመስተንግዶ) ሎት 9. ቋሚ ዕቃዎች ሎት 10. የህንፃ ቁሳቁሶች ሎት 11. የውሃ የመብራት የበር የመስኮት ጥገና ሎት 12. የተለያዩ የኮምፒውተር፣ የላፕቶፕ፣ የፕሪንተር የማባዣ፣ የፎቶ ኮፒ፣ የኢንተርኔት ዝርጋታ ጥገናዎች ሎት 13. የደንብ ልብስ ስፌት አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በማሟላት ለመወዳደር ይችላሉ።

1. የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑ ግብር የከፈሉ በአቅራቢ ዝርዝር ውሰጥ የተመዘገቡ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል።

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ የተመሰከረለት በእያንዳንዱ ሎት (CPO) 5000 (አምስት ሺህ ብር ብቻ ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማየት ናሙና የሚቀርብባቸውን እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ጨረታውን የሚያሸንፈው ድርጅት ዕቃዎችን እስከ ት/ቤቱ ድረስ ማድረስ አለበት።

5. ጨረታው አየር ላይ የሚቆይበት ግዜ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይሆንና በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ላይ ይከፈታል።

6. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተቋማት ራሳቸው አምርተው ለገበያ በሚያቀርቡት እቃ ወይም ምርት ካልሆነ በስተቀር የተዘጋጁ ዕቃዎችን ገዝተው ለሚወዳደሩበት እንደማንኛውም ተጫራቾች ጨረታ ሰነድ መግዛትና የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

7. ተጫራቾች ስርዝ ድልዝ የማይነበብ ሰነድ ጨረታ ላይ ያልተነበበ የዋጋ ማቅረቢያ ተቀባይነት አይኖረውም።

8. አሸናፊ ተጫራቾች ላለፉባቸው እቃዎች 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት (CPO) ማስያዝ አለባቸው።

9. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘውን ሰነድ የማይመለስ 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

10. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል እና ፎቶ ኮፒ ቫትን ጨምሮ በፖስታ ታሽጎ በፋይናንስ ክፍል በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 557 9371 እና 011 557 1602 በመደወል እንዲሁም በአካል

አድራሻ፡-

  • ግቢ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ጀርባ በሽታ ጤና ጣቢያ አጠገብ በመምጣት ማግኘት ይችላሉ።
  •  በአራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 08 መስከረም ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከስኛ ደ/ት/ቤት
  • ገቢ ገብርኤል ጀርባ ባሕታ ጤና ጣቢያ አጠገብ
  • ስልክ ቁጥር 011 557 9371 እና 011 557 1602

የመስከረም ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-04
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-04 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Meskerem One Kindergarten & Elementary School
  • Bid bond: 5000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T08:49:19.000Z
← Back to all tenders