Textile, Garment and Leather
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ትምህርት ጽ/ቤት የሚኪሊላንድ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 001/2019ዓ.ም
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ትምህርት ጽ/ቤት የሚኪሊላንድ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስከበሪያ በተጫረቱበት ዘርፍ የሞሉትን በባንክ በተረጋገጠ CPO ብቻ ማስያዝ አለባቸው::
1ኛ. ሎት 1 የደንብ ልብስ........................................................10,000/አስር ሺህ/0.5%/የተሰራ
2ኛ. ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች……….......................................10,000/አስር ሺህ/0.5%/የተሰራ
3ኛ. ሎት 3 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች…………………………………3,000/ሶስት ሺህ ብር/0.5%/የተሰራ
4ኛ ሎት 4 የጽዳት ዕቃዎች……………………………………………….5,000 /አምስት ሺህ ብር/0.5%/የተሰራ
5ኛ ሎት 5 ህትመት……………………………………………………….…150/መቶ አምሳ ብር/ 0.5% የተሰራ
6ኛ. ሎት 6 ቋሚ ለፕላት ለማሽነርሪ እና ለመሳሪያ መግዣ ዕቃዎች……12,500/አስራ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር /0.5% የተሰራ
7ኛ ሎት 7 የህከምና ዕቃዎች…………………………………………………..250/ሁለት መቶ አምሳ ብር/0.5% የተሰራ
8ኛ ሎት 8 ውሃ ቆሎ እና ኩከስ………………………………………………1,000/አንድ ሽህ ብር/0.5% የተሰራ
9ኛ ሎት 9 ለፕላንት ለማሽነሪ እና ለመሳሪያ እድሳት ጥገና………………400/አራት መቶ ብር /0.5% የተሰራ
በዚህ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይ መለያ(Tin) ቁጥር ያላቸው፡፡
3. የተጨማሪ እሴት ታከስ (የቫት) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
4. የአቅራቢዎች ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው እና በWWW.egP.ppa.gov.et የተመዘገቡ፡፡
5. ናሙና/ሳምፕል/ ለሚጠየቁ ዕቃዎች ማቅረብ የሚችል፡፡
6. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸው ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) የስራ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10% ባሸነፉባቸው ዕቃዎች ላይ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝና ተዋውለው ዕቃዎችን በትምህርት ቤቱ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙበት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቫትን ጨምሮ በመገለፅ ዋናውን እና ኮፒውን በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ሁለት እና ከሁለት በላይ የሆነ ፖስታ ከላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘውትር በስራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 6 ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ናሙናዎች ጨረታው ከመከፈቱ ከሁለት ቀን በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
9. በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጁ አካላት ከሆኑ በሚያመርቱበት ምርት ብቻ እና ሰነድ ለመውሰድ በሚመጡበት ጊዜ ከሚመለከተው አካል ወቅታዊ የሆነ፣ በጽ/ቤቱ ስም የተፃፈ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
10. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የሚኪሊላንድ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በመገኘት 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
11. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ላይ ያልቃል፡፡
12. ጨረታው በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ 4:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
13. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
14 ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ብርጭቆ ኮንዶሚኒየም ጊቢ ውስጥ
ስልክ ቁጥር 011-2-73-18-07 / 011-2-73-17-01
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በወረዳ 13 ትምህርት ጽ/ቤት
የሚኪሊላንድ አንደኛ እና መካከለኛ ደ/ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-04
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-04 10:30
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4:30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ketema Sub City Mikili Land Primary School
- Buyer address: ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ብርጭቆ ኮንዶሚኒየም ግቢ ውስጥ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T08:52:47.000Z