Spare Parts and Car Decoration Materials
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2019 በጀት ዓመት ጎማ፣ ከለመዳሪያና ፍላፕ ግዥ ለመፈፀም ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት (Specification) መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጎማ፣ ከለመዳሪያና ፍላፕ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢ.ግ.ሥ.ኮ/ብግጨ/01/2018/19
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2019 በጀት ዓመት ጎማ፣ ከለመዳሪያና ፍላፕ ግዥ ለመፈፀም ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘው መስፈርት (Specification) መሰረት ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ በዘርፉ ንግድ ፈቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር ለመክፈላችሁ ማስረጃ፣ የቫት ተመዝጋቢ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- እንዲሁም ከገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት በቃሊቲ ጉምሩክ ከባቡር መነሻ ፊት ለፊት በአዋሽ ባንክ በኩል ውስጥ ለውስጥ ገባ ብሎ በቀድሞ በግብርና ምርት ማሳደጊያዎች አቅርቦት ዘርፍ በሚገኘው ህንፃ 3ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 312 ግዥ ክፍል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ የጠቅላላውን ዋጋ 2% በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ (unconditional) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታ ዋጋ ለ30 (ሰላሳ) ቀናት የጸና መሆን ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የስብሰባ አዳራሽ ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ የመክፈቻ ስነሥርዓት ይከናወናል፡፡
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
ስልክ +251 911 984 467 ወይም +251 913 080 126
ፋክስ 0114 421 312
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን
Tender details
- Deadline: 2026-09-03
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-03 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Agricultural Business Corporation
- Buyer address: ከሳሪስ ፋፋ የምግብ አክሲዮን ማህበር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T08:54:12.000Z