Textile, Garment and Leather
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት ወረዳ 01 ስር የሚገኘው የድል በትግል ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማሰታወቂያ
የጨረታው ቁጥር 02/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት ወረዳ 01 ስር የሚገኘው የድል በትግል ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 ፡-የሰራተኛ የደንብ ልብስ
- ሎት 2 ፡- የቢሮ እቃዎች
- ሎት 3 ህትመት
- ሎት 4፡-አላቂ የትምህርት እቃዎች
- ሎት 5፡-የፅዳት እቃዎች
- ሎት 6፡-ቋሚ አላቂ እቃዎች
- ሎት 7፡- ቋሚ እቃዎች
- ሎት 8፡- ማሽን ጥገና
- ሎት 9፡- የመብራት እና ቧንቧ ጥገና ዝርጋታ
- ሎት 10፡- የጭነት እና ማጓጓዣ አገልግሎት መኪና
- ሎት 11፡- የሰራተኞች ካፌ
በዚህ ጨረታ ለመወዳደር የምትፈልጉና ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ህጋዊ ተወዳዳሪዎች፡-
1. በመንግስት ዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ የምስክር ወረቀት ያላቸው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
2. በጥቃቅን እና አነስተኛ በአምራችነት ተደራጅተው የሚመጡ ተወዳዳሪዎች በሚያቀርቡት የዋስትና ደብዳቤ መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
3. የእቃዎች ዋጋ 15% ቫት ተጨምሮ ይቅረብ : ባይቀርብ እንደ ተጨመረ ሆኖ የሚሰራ ይሆናል፡፡
4. ተጫራቾች የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ዝርዝር መረጃ የያዘ ሰነድ ከት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 4 በመምጣት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ መሙላት አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች ለሎት1፡-17,605 ለሎት2፡-1,600 ለሎት3፡-2,500 ለሎት4፡13,910 ለሎት5፡16,567 ለሎት6፡2,200 ለሎት7፡ 5,170 ለሎት8፡-3,000 ለሎት9፡ 3,000 ለሎት10፡2,000 የጨረታ ማስከበሪያ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች የተመረጡ እቃዎች እና ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን በቢሮ ቁጥር 05 ማስገባት ይችላሉ፡፡
9. አሸናፊ ሆነው የተመረጡ ድርጅቶች የአሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ የውል ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው፡፡
10. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሳቸው የትራንስፖርት ወጭ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማምጣት አለባቸው፡፡ት/ቤቱ ተጨማሪ በእቃዎች ላይ 20% የመጨመር ወይም የመቀነስ መብት አለው፡፡
11. ጨረታው ማስታወቂያው በወጣበት 10ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች ቢገኙም ባይገኙም ቢሮ ቁጥር 01 የሚከፈት ይሆናል፡፡
12. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ /አማራጭ/ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. በት/ቤቱ ሰራተኞች ካፌ ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች በራሳቸው የዋጋ መሙያ በሚሰጡት አገልግሎት ላይ የአንዱን ዋጋ ሞልተው ማስገባት አለባቸው
አድራሻ፡- ጉለሌ ክ/ከተማ ሽሮሜዳ ከስፔን ኤምባሲ አጠገብ
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0111-54-20-95
የድል በትግል ቅድመ አንደኛ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-03
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ጨረታው ማስታወቂያው በወጣበት 10ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-04 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው ማስታወቂያው በወጣበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Del Betegel Elementary School
- Buyer address: ጉለሌ ክ/ከተማ ሽሮ ሜዳ ከስፔን ኤምባሲ አጠገብ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T09:11:23.000Z