Textile, Garment and Leather

በጉለሌ ክ/ከተማ የእንጦጦ ፋና ጤና ጣቢያ የተለያዩ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም

በጉለሌ ክ/ከተማ የእንጦጦ ፋና ጤና ጣቢያ የተለያዩ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ሎት የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

የሎቶች እና የጨረታ ዋስትና መጠን

1. ሎት 1 -- የደንብ ልብስ -- 4,000 ብር (አራት ሺህ ብር)

2. ሎት 2 – የጽሕፈት መሣሪያ --4,550 ብር (አራት ሺህ አምስት መቶ ሃምሳ ብር)

3. ሎት 3 – የተለያዩ ሕትመቶች — 5,000 ብር (አምስት ሺህ ብር)

4 ሎት 4 – አላቂና ቋሚ የሕክምና ዕቃዎች - 5000 ብር (አምስት ሺህ ብር)

5. ሎት 5 – ሌሎች አላቂ የጽዳት ዕቃዎች -5,000 ብር (አምስት ሺህ ብር)

6. ሎት 6 -- ኤሌክትሮኒክስና ሕንፃ መሣሪያዎች - 500 ብር (አምስት መቶ ብር)

7. ሎት 7 – ቋሚ ዕቃዎች (ፈርኒቸር) – 2,000 ብር (ሁለት ሺህ ብር)

8. ሎት 8 – (የጀነሬተር ጥገና፣ ፍራጅ፣ ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ላፕቶፕ – 4,250 ብር (አራት ሺህ ሁለት መቶ ሃምሳ ብር)

9. ሎት 9 – ስፌት – 2,000 ብር (ሁለት ሺህ ብር)

10. ሎት 10 – ትራንስፖርት — 1000 ብር (አንድ ሺብር)

11. የህንጻ ጥገና ፕላንት ቁሳቁስ –20,000 (ሃያ ሺህ ብር )

12. ሎት የካፌ አገልግሎት 6000 (ስድስት ሺህ ብር)

13. ሎት የአንቡላንስ ጥገና – 2000 (ሁለት ሺህ ብር)

የጨረታ ተሳታፊዎች መስፈርቶች

1. ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN Number) ያላቸው መሆን አለባቸው። ከሀገር ውስጥ ባለሥልጣን የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።

2. ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው። እንዲሁም በጥቃቅን የተደራጁ ከሆኑ፣ ከደረጃቸው አካል የተሰጠ በሚሠሩት ሥራ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር ብቻ) በመክፈል፣ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በግዥ የሥራ ሂደት፣ 4ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 50 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ለሚያቀርቡባቸው ዕቃዎች በተናጠል ኦርጅናል እና ኮፒውን በመለየት፣ በታሸገ ኢንቨሎፕ የሚጫረቱበትን የዕቃ ዓይነት በመጥቀስ፣ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 50 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ሎት በጉለሌ ክፍለ ከተማ እንጦጦ ፋና ጤና ጣቢያ ስም በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና ወይም CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን ያጠቃለለ መሆን አለበት።

6. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸውን ዕቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10% (አስር በመቶ) የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

7. ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ዕቃ ወይም ናሙና በቅድሚያ ማቅረብ አለበት።

8. ጨረታ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ንብረት በራሱ ትራንስፖርት በውል መሠረት በተቋሙ ንብረት ክፍል ገቢ ሲያደርግ ያስያዘው ገንዘብ ይመለሳል።

9. ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ10ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ፣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በሥራ ቀናት በአዳራሸ ቁጥር 51 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ኮሚቴ ይከፈታል።

10. ለጨረታ ከቀረቡት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ መሥሪያ ቤቱ ከውል በፊት 20% የመቀነስ ወይም 20% ለመጨመር መብቱ የተጠበቀ ይሆናል። እንዲሁም ለካፌ ተጭራቾች ከስድስት ወር በፊት የዋጋ ማስተካከያ የማይደረግ መሆኑን እንገልጻለን። የቤት ኪራይና ውሃ መብራት ነጻ መሆኑን እንገልጻለን።

11. ተቋሙ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. አድራሻ: ሽሮሜዳ 31 ቁጥር ባስ ማዞሪያ፣ 400 ሜትር ወደ እንጦጦ ማርያም በሚወስደው መንገድ ላይ፣ ጉለሌ ክ/ከተማ አስተዳደር ወረዳ 1 ጽ/ቤት አጠገብ።

ስልክ ቁጥር፡ 011 154 0587 / 011 124 0272

በጉለሌ ክ/ከተማ የእንጦጦ ፋና ጤና ጣቢያ

በጉለሌ ክ/ከተማ የእንጦጦ ፋና ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-04
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ10ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት 11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-05 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Gulele Sub City Entoto Fana Health Post
  • Buyer address: ሽሮ ሜዳ 31 ቁጥር የከተማ አውቶቡስ ማዞሪያ ወደ እንጦጦ ማሪያም በሚወስደው መንገድ 400 ሜትር ከፍ ብሎ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አስተዳደር ጽ/ቤት አጠገብ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T12:18:57.000Z
← Back to all tenders