Products and Services
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሰት በዋግ ኸምራ ሰቆጣ ከተማ ዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዪን /ኃ/የተወሰነ / 10000/አስር ሺ ኩንታል ጥራት ያለዉ አፈርና ሌላ ባእድ ነገር የሌለዉ፤ ያልነቀዘ፤ መድሃኒት ያልገባበት/የተበጠረ/ ጥራቱን የጠበቀ ንፁህ ስንዴ በባለ 50 ኪሎ ግራም የተዘጋጀ ስንዴ ተቋሙ በሚያቀርበው የሰንዴ ናሙና መሰረት ማቅረብ ከሚችል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዘት ይ
Description
የሃገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሰት በዋግ ኸምራ ሰቆጣ ከተማ ዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዪን /ኃ/የተወሰነ።/ 10000/አስር ሺ ኩንታል ጥራት ያለዉ አፈርና ሌላ ባእድ ነገር የሌለዉ፤ያልነቀዘ፤ መድሃኒት ያልገባበት/የተበጠረ/ ጥራቱን የጠበቀ ንፁህ ስንዴ በባለ 50 ኪሎ ግራም የተዘጋጀ ስንዴ ተቋሙ በሚያቀርበው የሰንዴ ናሙና መሰረት ማቅረብ ከሚችል፤ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዘት ይፈልጋል
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።
1 በዘመኑ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለዉቸዉና የዘመኑ ግብርን የከፈሉ ለመሆናቸዉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና (የምትችል)
2ኛ በግልጽ ጨረታ ከሚገዛዉ ሰብል ጋር የተዛመደ ንግድ ስራ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት(Value Added Tax Certificate)ተመዝጋቢ የሆኑ የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት(Tax Payer identification Number) እንዲሁም ሌሎች ለጨረታው የሚጠቀሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል (የምትችል)
3. ተጨራቾች በግልጽ ጨረታ የሚገዛው ሰንዴ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ/ብር በመክፈል ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነድ ሰቆጣ ከተማ ወይብላ ማሪያም አጠገብ ከሚገኘው ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
4. ተጫራቾች በሌላ ዋጋ ተመስርቶ መወዳደር የማይቻል መሆኑንና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው አሸናፊው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት እንዲሁም የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ዋስትናው ውል ከተፈፀመበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 25 ቀናት ፀንቶ ሊቆይ የሚችል መሆኑን መገንዘብ ይኖርባችዋል
5. ተጫራቶች የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በተፈቀደላቸዉ በታወቁ ባንኮች ዋስትና (C.P.O) ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2 %ፐርስት በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (C.P.O) ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ /ዋናውን የገቢ ደረሰኝ /ከማወዳደሪያ ሃሳብ ጋር አብሮ ማስገባት ሲኖርባቸው በጨረታ ሰነዱ ከተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም።
6. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበትን ቀን አንስቶ ለተከታታይ 10/ አስር ተከታታይ ቀናት ድረስ ዘወትር በስራ ስዓት ሰነዱን በመግዛት የጨረታ ሃሳቡን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን በ11ቀን /አስረ አንደኛዉ ቀን / 3፡00 ድረስ ማስገባት ይኖርባችዋል።
7 የጨረታዉ ሰነድ ተጨራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት ዋቢ ሁለገብ /የገ/ህ/ስ/ማ ሃላፊነቱ የተወሰነ ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ 10 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ11/አስራ አደኛው ቀን /ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል በተገኙበት ከጥዋቱ 3፡00 ታሽገው ከጥዋቱ 3፡30 ጨረታው ይከፈታል። በጨረታ መክፈቻ ስርአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ አከፋፈት ባይገኙም በጨረታ አከፋፈት ስረአት ተገዥ ይሆናሉ ።
8. ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሃሳባቸውን ለማሻሻል ወይንም ከጨረታው ለመውጣት የፈለጉ እንደሆነ የጨረታ ማወዳደሪያ ሀሳብ ለማቅረብ ከተሰጣቸው 3 ቀን /ሶስት ቀን በፊት/ በፅሁፍ ሊያሳውቁ ይገባል።
9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባችዋል።
10. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዋግ ኽምራ ብሄረሰብ ዋቢ ሁለገብ የገ/ህ/ስ/ማህበር ኃላፊነት የተወሰነ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 440 1173 / 09 41 82 17 89 / 09 33 21 48 15 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ሰቆጣ ከተማ
ዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራት ዩኒዩን /ኃ/የተወሰነ
Tender details
- Deadline: 2026-09-04
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ 10 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ11/አስራ አደኛው ቀን /ከጥዋቱ 3፡00
- Bid opening: 2026-09-04 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ 10 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ11/አስራ አደኛው ቀን /ከጥዋቱ 3፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Wabi Farmers Cooperative Union
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T12:20:35.000Z