Spare Parts and Car Decoration Materials
በኦሮሚያ ከልላዊ መስተዳድር በጉጂ ዞን የኡራጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ አላቂ የፅሕፈት ዕቃዎች፣ አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ውሰጥ እቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች፣ የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ የቴክኒከና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ ነክ እቃዎችን፤ የተለያዩ የግንባታ እቃዎች እና የመሳሰሉትን ለ2019 ዓ.ም የበጀት አመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ከልላዊ መስተዳድር በጉጂ ዞን የኡራጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ አላቂ የፅሕፈት ዕቃዎች፣ አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ ቋሚ የቢሮ ውሰጥ እቃዎች፣ የመኪና ጎማዎች፣ የሰራተኞች የደንብ ልብስ፣ የቴክኒከና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ፣ ኤሌክትሮኒክስ ነክ እቃዎችን፤ የተለያዩ የግንባታ እቃዎች እና የመሳሰሉትን ለ2019 ዓ.ም የበጀት አመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በየንግድ መስኩ ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ፍቃዳቸውን፣ አመታዊ የስራ ግብር የተከፈለበትን፣ በመንግስት እቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበት እንዲሁም የተጨማሪ ስሴት ታክስ (ቫት)ና ቲን የተመዘገቡበትን የሚገልፅ መረጃ ሰነዶቻቸውን ፎቶ ኮፒውን ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቹን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ኡራጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.6 በመቅረብ የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ) ብር በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር ለጨረታው ከቀረበው ጠቅላላ ዋጋ 2% ለእያንዳንዱ የጨረታ ዓይነት በኡራጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በባንከ የተመሰከረለት ቼክ /CPO/ ወይም ጥሬ ገንዘብ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ማንኛውም ተጫራች እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) በማድረግ የጨረታ ዓይነቱን በግልጽ በመጻፍ ኮፒ እና ኦሪጂናሉን በመለየት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 5/1/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ኡራጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.6 በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
5. ጨረታው በ 5/1/2019 ዒ.ም ከቀኑ በ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት በኡራጋ ወረዳ ግንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁ.4 ይከፈታል::
6. አሸናፊው እንደታወቀ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል።
7. አሸናፊው ያሸነፋቸውን እቃዎች በሙሉ በራሱ ወጪ በማጓጓዝ ኡራጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግምጃ ቤት ማስገባት አለበት፡፡
8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁ 046 471-0190/191 ይደውሉ፡፡
በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር በጉጂ ዞን የኡራጋ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-15
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-09-15 14:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Uraga Wereda FEDB
- Bid bond: 2% ለእያንዳንዱ
- Bid document price: 400.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T12:22:04.000Z