Freight Transport

ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ልዩ ልዩ ወረቀቶችን የሚያጓጉዙለት የጭነት መኪናዎችን ውል ተፈራርሞ በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል

Description

የጭነት ማጓጓዝ የጨረታ ማስታወቂያ

ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር ልዩ ልዩ ወረቀቶችን የሚያጓጉዙለት የጭነት መኪናዎችን ውል ተፈራርሞ በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል፡፡

1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ሰርተፊኬት እና ሌሎችም የህጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶች ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች በቅድሚያ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ/ ቢሮ ቁጥር 101 በመክፈል ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ድረስ ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ በሚገኘው ቢሮአችን መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የዋጋቸውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች የሚያጓጉዙበትን መኪና የመጫን አቅም እና ዋጋቸውን በኪሎ ሜትር ስንት ብር እንደሆነ በመግለጽ በፖስታ አሽገው ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከግዥ ክፍል በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ፡፡

5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት በማህበሩ የስብሰባ አዳራሽ የግዢ ክፍል ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን በዝግ ቀን ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡

6. ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሽያል ሰነዳቸውን በአንድ ፖስታ አሽገው ማቅረብ ይችላሉ፡፡

7. ድርጅቱ ሌላ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ቦሌ ማተሚያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር

ስልክ ቁጥር 01115 15 50 05 / 0115 51 88 72

ፋክስ 0115 51 86 96

ፖ.ሳ.ቁጥር 2365

ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ

ቦሌ ማተሚያ ኃ.የተ.የግ.ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-09-08
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15ኛው ቀን ከረፋዱ 3፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-08 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው 15ኛው ቀን ከረፋዱ በ3፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Bole Printing P.L.C.
  • Buyer address: ቦሌ መንገድ ከቶታል ነዳጅ ማደያ ዝቅ ብሎ
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T13:07:02.000Z
← Back to all tenders