Spare Parts and Car Decoration Materials
የሐረሪ ጤና ጥበቃ ቢሮ ለ2019 በጀት አመት ለቢሮው ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል የመኪና መለዋወጫዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሐረሪ ጤና ጥበቃ ቢሮ ለ2019 በጀት አመት ለቢሮው ተሽከርካሪዎች አገልግሎት የሚውል የመኪና መለዋወጫዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የማይመለስ 500.00 ብር/ አምስት መቶ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሐረሪ ጤና ጥበቃ ቢሮ የፋይናንስ ክፍል መውሰድ ትችላላችሁ።
የዘመኑ የታደሰ የንግድ ህጋዊ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት የአቅራቢነት ምዝገባ ማስረጃ እና ሌሎች በጨረታ ሰነዱ የተጠየቁ ከስራው ጋር የተያያዙ ሰነዶችን ከጨረታው መልስ ጋር ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (ጥሬ ገንዘብ ክፍያ ማዘዣ) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በሐረሪ ጤና ጥበቃ ቢሮ ስም ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
2. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ለ60 ቀናት ይሆናል።
3. ተጫራቾችይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዳቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
4. የጨረታው ዓይነት HRHB/001/19 ባለ አንድ ኤንቨሎፕ ሲሆን ተጫራቾች ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ሰነዶቻቸውን በጨረታ መመሪያው መሠረት በማያያዝ አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
5. ጨረታው የሚከፈተው ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4:15 ተዘግቶ በእለቱ 4:30 በጽ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል።
6. ከላይ የተጠቀሱት ቀናት በአላት ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።
7. መ/ቤቱ አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
8. የመስሪያ ቤቱ አድራሻ፡- ሐረር ጂኔላ ወረዳ ወደ ጅጅጋ በሚወስደው መንገድ የመከላከያ ኮንዶሚኒየም ጎን ጨረታው የሚከፈትበት ቦታ፡- የሐረሪ ጤና ጥበቃ ቢሮ አንደኛ ፎቅ በሚገኘው አዳራሽ
9. ለበለጠ መረጃ እባክዎን በስልክ ቁጥር 09 13 89 07 51 ይደውሉ።
የሐረሪ ጤና ጥበቃ ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-09-11
- Bid closing time: 10:15
- Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4:15
- Bid opening: 2026-09-11 10:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4:30
- Region: Hareri
- Publishing entity: የሐረሪ ጤና ጥበቃ ቢሮ
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T13:13:25.000Z