House Furniture

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ሆነ ቀርጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2019 በጀት አመት የሚያገለግሉ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ሆነ ቀርጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች ለ2019 በጀት አመት የሚያገለግሉ 

የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎች

1. የተለያዩ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች

2. ፈርኒቸሮች

3. ኤሌክትሮኒክስ

4. የጽህፈት መሳሪያዎች

5. የጽዳት መሳሪያዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በዘርፍ የስራ ፍቃድ ያላቸው ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት ካሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. ተጫራቾች ህጋዊ የታደሰ የሥራ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ።

2 ተጫራቾች ለተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 (አሥራ አምስት) የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 1500 በመክፈል በቀርጫ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000 (አስር ሺህ) ባንክ በተመሰከረለት ቼክ(CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ከኦርጅናል ጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡

5. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በግልጽ በመጻፍ ኮፒና ኦርጅናሉን በመለየት ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።

6. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚሆን ሲሆን በ11ኛው ቀን 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት በቀርጫ ወረዳ ገንዘብ/ጽ/ቤት ይከፈታል።

7. አሸናፊው አካል እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊ ወዲያውኑ ይመለሳል፡፡

8. አሸናፊ በጨረታ መመሪያ መሰረት አሸናፊነቱ በጽሁፍ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ በ10/ቀን ውስጥ ለጨረታ ውል ማስከበሪያ የሚውል ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ ቼክ (CPO) ወይም ጥሬ ገንዘብ በማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል መፈራረም አለበት።ይህ ባይፈጸም ቀደም ሲል ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

9. ያሸነፉትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ መ/ቤቱ ግምጃ ቤት ማምጣትና ፈርኒቸር ዕቃዎችን በራሱ ወጪ ማጋጣጠም የሚችል።

10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ:-ሞባይል ቁጥር 0905 873 056 / 0918 952 198

በኦሮሚያ ክልል የምዕራብ ጉጂ ዞን ቀርጫ ከተማ ገንዘብ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-07
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚሆን ሲሆን በ11ኛው ቀን 3፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-07 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚሆን ሲሆን በ11ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Guji Zone Kercha Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 1,500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 26, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T13:27:50.000Z
← Back to all tenders